በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቤቶቻቸው እየፈረሱ መሆኑን ማይ ካድራ የሚኖሩ ተናገሩ


የትግራይ ክልል ካርታ /ከጉግል ማፕ የተገኘ/
የትግራይ ክልል ካርታ /ከጉግል ማፕ የተገኘ/

በምዕራባዊ ትግራይ ዞን ማይ ካድራ ከተማ ላለፉት ሃያ ዓመታት ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ቤቶቻቸው በአካባቢው ባለሥልጣናት እየፈረሱባቸው መሆናቸውን እየገለፁ ነው።

በምዕራባዊ ትግራይ ዞን ማይ ካድራ ከተማ ላለፈት ሃያ ዓመታት ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ቤቶቻቸው በአካባቢው ባለሥልጣናት እየፈረሱባቸው መሆናቸውንና ያለመጠለያ መቅረታቸውን እየገለፁ ነው።

አቤቱታቸውን የሚሰማቸው ማጣታቸውንና ከመካከላቸው የታሠረ ሰውም እንዳለ አመልክተዋል።

በድርቅ ምክንያት ያለሰብል መቅረታቸውንና እርዳታም እንደማያገኙ ተናግረዋል።

በአካባቢያቸው ሙስና መንሠራፋቱን ነዋሪዎቹ የሚናገሩ ሲሆን ሕገወጥ አስተላላፊዎች ብዙ ወጣቶችን እያስወጡ መሆናቸውንና አንዳንድ በፖሊስና በመንግሥቱ መዋቅር ውስጥም ለአስተላላፊዎቹ ድጋፍና ከለላ የሚሰጡ መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ቅሬታዎቻቸውን ሲያቀርቡ የተለያዩ የፖለቲካ ፍረጃዎች እንደሚካሂዱባቸው አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላት ለአቤቱታ አዲስ አበባ ገብተው ከትናንት፤ ረቡዕ ጀምሮ እዚያው ቢገኙም የፌደሬሽን ምክር ቤቱን አፈ ጉባዔ ለማግኘት እንዳልተሣካላቸው ገልፀዋል።

ከባለሥልጣናቱ ምላሽ ለማግኘት እየጣርን እንገኛለን፤ ለዛሬ ያደረግናቸው ጥረቶች አልተሣኩም።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ቤቶቻቸው እየፈረሱ መሆኑን ማይ ካድራ የሚኖሩ ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:25 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG