በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሞተውን ሰው ማንነት ወዲያውኑ ለቤተሰብ ማሳወቅ ይገባ ነበር


ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎ
ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎ

ቅዳሜ ዕለት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሞተውን ሰው ማንነት ወዲያውኑ ለቤተሰብ ማሳወቅ ይገባ እንደነበር ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፍ ሕጎች ጠቅሰው አቶ ሽብሩ በለጠ የተባሉ የሕግ ባለሞያ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። የእስረኛ ቤተሰቦች በበኩላቸው ዛሬም ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ ማወቅ እንዳልቻሉ ይናገራሉ።

ቅዳሜ ዕለት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሞተውን ሰው ማንነት ወዲያውኑ ለቤተሰብ ማሳወቅ ይገባ እንደነበር ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፍ ሕጎች ጠቅሰው አቶ ሽብሩ በለጠ የተባሉ የሕግ ባለሞያ ለአሜሪካ ተናገሩ።

በሌላ በኩል፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች፣ ታሳሪ ቤተሰቦቻቸው የት እንደሚገኙ እስከ ዛሬ ማወቅ አልቻሉም። ያነጋገርናቸው የታሳሪ ቤተሰቦች እንደነገሩን ከሆነ፣ "እስከ ዐርብ ጠብቁ" ነው የተባሉት። ሊጠይቁ ሲሄዱም ሆነ ጥያቄ ሲያቅቡ የሚደርስባቸው እንግልት ዛሬም ቀጥሏል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የወጣቶች ክፍል ኃላፊ አቶ ጉርሜሳ አያና ባለቤት ወ/ሮ ዐይናለም ደበላ፤ የአንድ ልጃቸውን አባት ይኑር ይሙት አለማወቅ እንዳስጨነቃቸው ይናገራሉ። “እንግዲህ ከቤት በሰላም ተጠርቶ ለጥያቄ ነው የምትፈለገውተብሎ ተወስዶ እስር ቤት ውስጥ ተቃጥሎ የሚሞትበት ሀገር ላይ ያለነው” ሲሉ ይናገራሉ።

እናቶች ልጆቻቸውን ፍለጋ ወገባቸውን በመቀነት አስረው በጉልበታቸው እየሄዱ እንደሚገኙ ወ/ሮ ዐይናለም አክለው ይናገራሉ።

በእሥር ላይ የነበሩ 23 ሰዎች በቃጠሎው መሞታቸውን በትናንቱ ዕለት ይፋ ያደረጉት የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽ/ቤት ቃል አቀባይ አቶ መሃመድ ሰዒድ “የሟቾቹ ማንነት ደረጃ በደረጃ ለቤተሰቦቻቸው ይገለፃል” ብለው ተናግረዋል።

የድምጽ ፋይሉን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የሞተውን ሰው ማንነት ወዲያውኑ ለቤተሰብ ማሳወቅ ይገባ ነበር
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:43 0:00

በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊው ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ እናት ወ/ሮ ሙጪት ተካ ልጃቸው ያለበትን ባለማወቃቸው ጭንቀት ላይ መሆናቸውን እንዲሁም የአቶ በቀለ ገርባ ልጅ ወ/ት ቦንቱ በቀለ፣ የአቶ ደጀኔ ጣፋ ባለቤት ወ/ሮ አሰለፈች ሙላትና የመኢአድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አሰጋ አሰፋ ልጅ ወ/ት ህይወት አሰፋ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ሁኔታ አለማወቃቸው ጭንቀት ውስጥ እንደከተታቸው ለአሜሪካ ድምፅ መግለፃቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG