በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲስ በተዋቀረው ካቢኔ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች (ክፍል ሁለት)


ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፡ ፎቶ ፋይል
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፡ ፎቶ ፋይል

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የዛሬ ዓመት አዋቅረውት የነበረውን ካቢኔ ከንድ ዓመት በኋላ አፍርሰው 21 አዳዲስ ሹመቶች የተካተቱበትና የቀድሞ ዘጠኝ ሚኒስተሮችን ባሉበት የሚያቆይ አዲስ ካቢኔ በትናንትናው ዕለት ማዋቀራቸው ይታወሳል። እኛም በትናንትናው ዕለት የተለያዩ ሰዎችን አስተያየት ጠይቀን ማስተላለፋችን ይታወሳል በዛሬው ዕለት በገባነው ቃል መሰረት ሁለትኛውን ክፍል ይዘናል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሶቹ ተሿሚዎች የዕድገት ደረጃው የሚጠይቀው ዝንባሌ፥ እውቀትና ክህሎት ያላቸው እንደሆኑ ሹመቱን ባፀደቁበት ወቅት ተናግረዋል።

ይህ ሹመትና አዲስ የካቢኔ አወቃቀር በኢትዮጵያ እየተነሱ ላሉት ችግሮች መፍትሄ ይሰጣል ወይ? በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ የተካተቱት የሚኒስትሮች ቁጥር የበዛውን የኦሮሞ ተወላጆች መያዛቸው ለሥልጣን ክፍፍሉ የብሔር ተመጣጣኝነት መልስ ይሰጣል ወይ? በሚል ላነሳናቸው ጥያቄዎች አስተያየት ሰጪዎችቹ ሐሳባቸውን አካፍለዋል።

ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

አዲስ በተዋቀረው ካቢኔ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች (ክፍል ሁለት)
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:01 0:00

XS
SM
MD
LG