በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዶ/ር መረራ መታሠር ላይ የተለያዩ ወገኖች አስተያየት


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር መታሠር “ኢትዮጵያ ያወጀችው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ምናልባት ተቃውሞን ዝም ለማሰኘትና በሕገመንግሥት የተረጋገጡ የኢትዮጵያን ዜጎች መብቶች ለመንፈግ ጉዳይ እየዋለ ለመሆኑ ያለንን ሃሣብ ይበልጥ ያጠናክረዋል” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምክትል ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡

ምክትል ቃል አቀባዩ ማርክ ቶነር ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል የዶ/ር መረራ ጉዲና መታሠር ዜና መንግሥታቸውን ያሳሰበ መሆኑንና የኢትዮጵያ መንግሥት በዶ/ር መረራ ላይ ያለውን ክሥ ሁሉ ለሕዝብ ግልፅ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ “ኢትዮጵያ የመጨረሻውን ሕጋዊ ነፃ የኦሮሞ ተቃዋሚ ድምፅ ዘጋች” ሲል የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር መግለጫ አውጥቷል፡፡

የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ዶ/ር በያን አሶባ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ዶ/ር መረራ ጉዲና ሃሣባቸውን የመግለፅ መሠረታዊ ሰብዓዊና በሕገ መንግሥት የተደነገገ መብታቸውን ነው የተጠቀሙት” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ዶ/ር መረራ የታሠሩት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ የተደነገገ አንቀፅ በመተላለፋቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በዶ/ር መረራ መታሠር ላይ የተለያዩ ወገኖች አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:05 0:00
በዶ/ር መረራ መታሠር ላይ ከኦዲኤፍ አመራር አባል ዶ/ር በያን አሶባ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:20 0:00

XS
SM
MD
LG