በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቦረና ዞን በሦስት ወረዳዎች የተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች


በኦሮምያ ክልል የቦረና ዞን ሦስት የተለያዩ ወረዳዎች ነዋሪዎች በትላንት እና በዛሬው ዕለት የተቃውሞ ሰልፎችን ማካሄዳቸው ተዘገበ።

በኦሮምያ ክልል የቦረና ዞን ሦስት የተለያዩ ወረዳዎች ነዋሪዎች በትላንት እና በዛሬው ዕለት የተቃውሞ ሰልፎችን ማካሄዳቸው ተዘገበ።

ተቃውሞ ሰልፎቹ ዛሬ በዱብሉቅ ወረዳ ትላንት ደግሞ በያቤሎና በሚዮ ወረዳዎች በተመሳሳይ መካሄዳቸውን ነው ነዋሪዎቹ የተናገሩት።

የልዩ ኃይልና የመከላከያ ሠራዊት አባላት እያደረሱብን ነው፤ ያሏቸው ጥቃቶች እንዲቆሙና ካሁን ቀደም ለደረሱ ጉዳቶች ተጠያቂ የሆኑ ወገኖችም ለፍርድ ይቅረቡ የሚሉት ሠልፈኞቹ ካነሷቸው ጥያቄዎች ውስጥ መሆናቸውም አስረድተዋል።

በተጠቀሱት የመንግሥት ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ153 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውንና በርካቶች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የዞኑ የኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገልማ ቦሩ ለአሜሪካ ድምፅ የኦሮምኛ ክፍል ባልደረባችን ሶራ ሃላኬ ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በቦረና ዞን በሦስት ወረዳዎች የተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:48 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG