በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የአማራ ፋኖ “የሰላም ጥሪ አልተደረገልንም” አሉ


የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የአማራ ፋኖ “የሰላም ጥሪ አልተደረገልንም” አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:10 0:00

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የአማራ ፋኖ “የሰላም ጥሪ አልተደረገልንም” አሉ

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የአማራ ታጣቂ ፋኖ፣ የኢትዮጵያ ኹሉን አቀፍ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ወደ ሰላም ሊያመጣ የሚችል ሕጋዊ ተቋም መኾኑን እንደማይቀበሉት፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ሁለቱም አካላት፣ ኮሚሽኑ ሲዋቀር አንሥቶ ምንም ዓይነት ተሳትፎ አለማድረጋቸውን፤ እንዲሁም ኮሚሽኑ በመንግሥት በጀት የሚንቀሳቀስ መኾኑን በመጥቀስ፣ በገለልተኛነቱ ላይ ጥያቄ አንሥተዋል፡፡ በተጨማሪም፣ ሕጋዊ በኾነ መልኩ በደብዳቤም ይኹን በኢ-ሜይል በምክክር መድረኩ ላይ እንዲሳተፉ አለመጋበዛቸውን፣ ተወካዮቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዪ ለሁለቱም በትጥቅ ትግል ላይ ለሚገኙ አካላት በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ከተላለፈው ሀገራዊ ጥሪ በተጨማሪ የተላከ ደብዳቤ አለመኖሩን ገልጸው ይሄ የሆነው ሁለቱም ህጋዊ ቢሮ ስለሌላቸው መሆኑን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG