በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሰተኞችን ለመታደግ የሚደረገው ጥረት በባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች መስተጓጎሉ ተገለፀ


ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ፍልሰተኞች በጀልባ ተጭነው ወደ አውሮፖ እየተጓዙ
ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ፍልሰተኞች በጀልባ ተጭነው ወደ አውሮፖ እየተጓዙ

በሜዲትራኒያን ባሕር ላይ ለአደጋ የተጋለጡ ፍልሰተኞችን በማዳን ሥራ በተሰማሩ ሠራተኞች ላይ የሊቢያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች የሚሰዝሯቸው የማስፈራሪያ ጥቃቶች፣ ለአንድ ፍልሰተኛ ህይወት ማለፍ ምክኒያት እንደሆነ የጀርመን የበጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ።

ኤስኦኤስ ሂውማኒቲ የተሰኘው በሰብአዊነት ላይ የሚሠራው የጀርመን በጎ አድራጎት ድርጅት፣ ቅዳሜ ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ የሊቢያ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች፣ ለሕይወት አስጊ በሆነው የነፍስ ማዳን ሥራ ወቅት ተኩስ በመክፈታቸው ምክኒያት በተቀሰቀሰ ሁከት ለአደጋ የተጋለጡ ፍልሰተኞችን የማዳን ሥራን ማስተጓጎላቸውን ገልጿል።

ድርጅቱ ሦስት በአግባቡ ባልተሠሩ ጀልባዎች ላይ ተሳፍረው ወደ አውሮፓ ለማቅናት ጥረት በማድረግ ላይ ከነበሩት ፍልሰተኞች በርካቶቹ ወደ ባሕሩ ለመዝለል መገደዳቸውን አመልክቷል።

በነፍስ አድን ጥረቱ 77 ፍልሰተኞችን መታደግ መቻሉን እና ቁጥራቸው የበዛ ሌሎች በኃይል ከሊቢያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ጀልባ ላይ እንዲሳፈሩ መደረጋቸውን አክሎ ገልጿል። በዚህም ምክኒያት ስድስት የቤተሰብ አባላት መነጣጠላቸውን አስታውቋል። የሊቢያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ቃል አቀባይ ስለ ጉዳዩ እንዲያብራሩ ለተደረጉላቸው የስልክ ጥሪዎች እና የኢሜል መልዕክቶች ምላሽ አልሰጡም።

በተያያዘ ባለፈው የአውሮፓውያኑ 2023 ከሊቢያ የተነሱ 962 ፍልሰተኞች ባሕር ላይ መሞታቸው እና ቁጥራቸው 1ሺህ563 የሚደርሱት የገቡበት ሳይታወቅ መቅረቱን ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት አይኦኤም አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG