በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ጫካ”ው በመባል የሚታወቀው የካሊ የስደተኞች መንደር ከነገ ጀምሮ መፍረስ ይጀምራል

ሻንጣዎችንና የግል ንብረታቸውን የተሸከሙ ወንዶችና ሴቶች ካሌስ ከተባለቸው የሰሜን ፈረንሳይ ወደብ ከተማ ከሚገኘው የስደተኞች ሰፈር እየወጡ ናቸው።
ሻንጣዎችንና የግል ንብረታቸውን የተሸከሙ ወንዶችና ሴቶች ካሌስ ከተባለቸው የሰሜን ፈረንሳይ ወደብ ከተማ ከሚገኘው የስደተኞች ሰፈር እየወጡ ናቸው።

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች “ካሊ በተባለችው የሰሜን ፈረንሳይ ወደባዊት ከተማ ከሚገኘው የስደተኞች ሰፈር ለቀው እየወጡ ነው። ይህ ጫካው የሚል መጠሪያ ያተረፈው የስደተኞች መንደር ከነገ ጀምሮ መፍረስ እንደሚጀምር እየተነገረ ይገኛል።

ወደ 8 ሺሕ የሚጠጉ ስደተኞች በአስከፊ ሁኔታ እንደሚኖሩበት በሚነገረው በዚህ የስደተኛ ሰፈር ከኢትዮጵያ፣ከኤርትራ እና ከአፍጋኒስታን የተሰደዱ ስደተኞች ይገኙበታል።

ከኢትዮጵያ የሚሆኑትን በአስከፊ ሁኔታ የሚኖሩትን ስደተኞች ወደ ሌሎች የስደተኞች ሰፈሮች የማዛወሩ ሂደት አንድ ሳምንት ያህል ሊወስድ ይችላል።

ፍልሰተኞቹ በፈረንሳይ ዙርያ በሚገኙ የስደተኞች ሰፈሮች እንዲሰፍሩ ይደረጋል። ጥገኝነት የመጠየቅ እድልም ይሰጣቸዋል ተብሏል። ይሁንና አንዳንዶቹ ስደተኞች በእንግሊሽ ቻነል በኩል ወደ ብሪታንያ መዝለቅ ስለሚፋልጉ ወደተባሉት ሰፈሮች አንሄድም ሊሉ ይችልሉ የሚል ስጋት አለ።

“ጫካ”ው በመባል የሚታወቀው የካሊ የስደተኞች መንደር ከነገ ጀምሮ መፍረስ ይጀምራል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:19 0:00

XS
SM
MD
LG