በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጣልያን ጠ/ሚ ለፍልስተኞች ቀውስ ዓለም አቀፍ ዕርዳታ እንደሚጠይቁ አስታወቁ


ፎቶ ፋይል፦ የጣልያን  ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጅያ ሜሎኒ
ፎቶ ፋይል፦ የጣልያን  ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጅያ ሜሎኒ

የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጅያ ሜሎኒ “ከአረመኔነት እና ባርነት” ጋር ተመሳሳይ ሆኗል ሲሉ ለገለጹት የሀገራቸው የፍልስተኞች ቀውስ፣ ዓለም አቀፍ ዕርዳታ እንደሚጠይቁ አስታወቁ።

ሜሎኒ ነገ ሐሙስ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ጥሪውን ያቀባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቁጥሩ እየጨመረ ከመጣው ፍልስተኞች ጋር እየታገለ የሚገኘው የጣልያን መንግሥት ከትናንት በስቲያ ሰኞ፣ ፍልሰተኞቹ ታስረው የሚቆዩበት ጊዜ እንዲራዘምና፣ በሀገር ውስጥ ለመቆየት ሕጋዊ መብት የሌላቸው በርካቶች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የሚያስችል እምርጃዎችን መውሰዱን የመንግሥት ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡፡

ውሳኔው የመጣው ባላፈው ሳምንት ወደ 10ሺየሚጠጉ ፍልስተኞች ደቡብ ጣልያን ደሴት ላምፔዱሳ ከደረሱ በኋላ ነው፡፡ ክስተቱ፣ ባላፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ህገ ወጥ ፍልስተኞችን ለመግታት ቃል ገብተው የነበሩት ቀኝ አክራሪዋ ሜሎኒን ተአሚንነት ትልቅ አደጋ ውስጥ መጣሉ ተመልክቷል፡፡

በዚህ ዓመት እስካሁን ወደ 130ሺ የሚጠጉ ፍልስተኞች ጣልያን መግባታቸውን ከመንግሥት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ይህ እ.ኤ.አበ 2022 ከነበረው ተመሳሳይ ጊዜ እጥፍ ያህል መሆኑ ተገልጿል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG