በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዕድል እንዲሰጥ የሀገሪቱ መሪዎች ጥሪ እያቀረቡ ነው


ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር በዋይት ሃውስ ኦቫል አፊስ(በቤተመንግሥቱ የፕሬዚዳንት ቢሮ)
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር በዋይት ሃውስ ኦቫል አፊስ(በቤተመንግሥቱ የፕሬዚዳንት ቢሮ)

የዶናልድ ትረምፕ ፕሬዚዳንትነት ሆነው መመረጥ አልዋጥ ያላቸው በሽሕዎች የተቆጠሩ አሜሪካዊያን ሠላማዊ ሰልፎች ሲያካሂዱ፤ የዴሞክራቶቹ ዕጩ ሂላሪ ክሊንተን የሃሳብ ልዩነቶች ቢኖርም ደጋፊዎቻቸው ለአዲሱ ፕሬዚዳንት ዕድል እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

ማክሰኞ ዕለት ፕሬዚዳንታቸውን የመረጡት አሜሪካዊያን ረጅም ጊዜ ከፈጀውና መከፋፈልን ከፈጠረው የምርጫ ሂደት በፍጥነት በማገገም ለቀጣዩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እድል እንዲሰጡና አብሮነታቸውን እንዲያጠናክሩ የሀገሪቱ መሪዎች እየወተወቱ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የትረምፕ ፕሬዚዳንትነት ሆነው መመረጥ አልዋጥ ያላቸው በሽሕዎች የተቆጠሩ አሜሪካዊያን የተቃውሞ ሠላማዊ ሰልፎች አካሂደዋል።

ዶናልድ ትራምፕን በመቃወም የተካሄደ ሠላማዊ ሠልፍ
ዶናልድ ትራምፕን በመቃወም የተካሄደ ሠላማዊ ሠልፍ

በትናንትናው ዕለት የዶናልድ ትረምፕን አሸናፊነት በህዝብ ፊት አምነው የተቀበሉት የዴሞክራቶቹ ዕጩ ሂላሪ ክሊንተን የሃሳብ ልዩነቶች ቢኖርም ደጋፊዎቻቸው ለአዲሱ ፕሬዚዳንት ዕድል እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

ሂላሪ ክሊንተን
ሂላሪ ክሊንተን

“ሀገራችን የገባችበትን ጥልቅ መከፋፈል አስተውላችኋል? አሁንም ግን በአሜሪካ እምነት አለኝ፡፡ ሁልጊዜም ይኖረኛል፡፡ እናንተም ተመሣሣይ አስተሳሰብ ካላችሁ ውጤቱን ተቀብላችሁ የወደፊቱን አስተውሉ፡፡ ዶናልድ ትረምፕ ፕሬዚደንታችን ይሆናሉ፡፡ የመሪነት ዕድል እንዲያገኙ መፍቀድና አይኖቻችንን ገልጠን የሚሠሩትን መመርመር ይገባናል እላለሁ፡፡” ብለዋል ሚስ ክሊንተን በንግግራቸው፡፡

የቪኦኤ ዘጋቢዎች ከኒውዮርክና ዋሽንግተን ዲሲ ያስተላለፏቸውን ዘገባዎች ሔኖክ ሰማእግዜር ያቀርበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ለአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዕድል እንዲሰጥ የሀገሪቱ መሪዎች ጥሪ እያቀረቡ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:50 0:00

XS
SM
MD
LG