በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በታንዛኒያ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ155 ሰዎች ህይወት አለፈ


የሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ በጎርፍ ተይዘው ዳሬ ሳላም፣ ታንዛኒያ እአአ ሚያዚያ 25/2024
የሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ በጎርፍ ተይዘው ዳሬ ሳላም፣ ታንዛኒያ እአአ ሚያዚያ 25/2024

በታንዛኒያ ለሳምንታት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ምክንያት የ155 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሙስ እለት አስታወቁ።

በተለይ በባህር ድርቻ አካባቢ በሚገኙ ከተሞች እና በዋና ከተማው ዳሬ ሳላም የዝናብ መጠኑ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የተመዘገበው የሞት ቁጥር፣ ከሁለት ሳምንት በፊት ከተዘገበው ሞት ከእጥፍ በላይ የጨመረ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃሲም ማጃሊዋ ለፓርላማ እንደተናገሩት፣ የኤል ኒኖ የአየር ንብረት ሁኔታ እየቀጠለ ያለውን የዝናብ ወቅት ማባባሱን እና ከፍተኛ ጎርፍ ማስከተሉን ገልጸው፣ መንገዶችን፣ ድልድዮችን እና የባቡር ሀዲዶችን ማፈራረሱን አመልክተዋል።

በጎርፍ የተጥለቀለቁ ትምህር ትቤቶች የተዘጉ ሲሆን፣ የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶች በጎርፍ ውሃ የተጎዱ ሰዎችን በመታደግ ላይ ናቸው።

ማጃሊዋ አክለው ዝቅተኛ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ከፍታ ወዳላቸው ቦታዎች እንዲሄዱ አስጠንቅቀው፣ የየክፍለከተማው ባለስልጣናት ቤታቸው በጎርፍ ለተወሰደባቸው ሰዎች አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያደርሱ አሳስበዋል።

እስካሁን ከ51ሺህ በላይ አባወራዎች በዝናብ መጎዳታቸውንም አመልክተዋል።

በጎረቤት በሚገኙት ብሩንዲ እና ኬንያም በተመሳሳይ ሁኔታ የጎርፍ አደጋ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፣ በኬንያ እስከ ሰኞ ባለው ጊዜ ድረስ 35 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG