በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ጉዳይ ዓለምአቀፍ ድምፆች


በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውጊያውን ሸሽተው ወደሱዳን የተሰደዱ
በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውጊያውን ሸሽተው ወደሱዳን የተሰደዱ

ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ሁኔታ በብርቱ እያሰጋቸው መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽና የድርጅቱ የሰብዓዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሸሌ ተናግረዋል።

ሁለቱ የመንግሥቱቱ ድርጅት ኃላፊዎች ትናንት በተናጠል ባወጧቸው መልዕክቶች በግጭቱ ውስጥ ያሉ ወገኖች ሁሉ ለሲቪሎች ሙሉ ጥበቃ እንዲያደርጉና ለሰብዓዊ አቅርቦቶች ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ አካባቢውን ማናጋት መጀምሩ አስግቶኛል ያሉት የአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ተጠሪና ምክትል ፕሬዚዳንት ዮሴፕ ቦሬል ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ትናንት ብራስልስ ላይ ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ ሦስተኛ እያስቆጠረ ባለው ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች ሁሉ ህፃናትን እንዲታደጉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የህፃናት ደራሽ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ አሳስቧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በኢትዮጵያ ጉዳይ ዓለምአቀፍ ድምፆች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:10 0:00


XS
SM
MD
LG