በጎንደር አድማው ዛሬም መቀጠሉንና ባሕር ዳር ላይ ግን ሥራዎች ክፍት ሆነው መዋላቸውን ከየከተሞቹ ነዋሪዎችና የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት የደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
በሌላ በኩል ግን ቡሬ ዳሞት ላይ የተኩስ ልውውጥ እንደነበረና በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሥራ የማቆምና የሰልፍ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውም ተገልጿል፡፡
ስለተባሉት የክልሉ ሁኔታዎች ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለዛሬ ምላሽ ለማግኘት ያደረግናቸው ጥሪዎች አልተመለሱም፤ የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ ትናንት በሰጡት ምላሽ ግን ፍኖተ ሰላምና ጎንደር ላይ ካሉት ሁኔታዎች በስተቀር ክልሉ በአመዛኙ ሰላማዊ መሆኑን ገልፀው ነበር፡፡
ለተጨማሪ ዘገባና ዝርዝር መረጃዎች ከዚህ ጋር የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡
አቶ ሙሉጌታ አበበ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ ምክትል ፕሬዚዳንት በአማራ ክልል የሐሙስና የዓርብ ሁኔታ ላይ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ
በጎንደርና በአካባቢዋ የሐሙስና የዓርብ ሁኔታ ላይ ከአንድ የጎንደር ነዋሪ የተደረገ ቃለ-ምልልስ
በባሕር ዳርና በአካባቢዋ የሐሙስና የዓርብ ሁኔታ ላይ ከአንድ የባሕር ዳር ነዋሪ የተደረገ ቃለ-ምልልስ