በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድርቁ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አለመጉዳቱን መንግሥቱ አስታወቀ፤ የአይኤምኤፍ ሪፖርት ተቃራኒ ነው


ዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት - አይኤምኤፍ በየዓመቱ በሚያወጣው የአጠቃላይ ምጣኔ ኃብት ዕድገት ሪፖርቱ የኢትዮጵያ የምርት ዕድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል አመልክቷል።

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ዓመታዊ ምርት ኤልኒኞን ተከትሎ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት እንደማይቀንስ የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር አስታውቋል።

“ድርቅ ባልተከሰተባቸው አካባቢዎች የተከናወነው የማካካስ ሥራ የምርት መጠን እንዳይቀንስና እንደተለመደው 270 ሚሊዮን ኩንታል እንዲሆን አስችሏል” ብለዋል የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ብርሃኑ።

በሌላ በኩል ደግሞ ዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት - አይኤምኤፍ በየዓመቱ በሚያወጣው የአጠቃላይ ምጣኔ ኃብት ዕድገት ሪፖርቱ የኢትዮጵያ የምርት ዕድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል አመልክቷል።

በያዝነው የአውሮፓ 2016 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኃብት ምጣኔ በ4.5 ከመቶ እንደሚያድግ የገንዘብ ድርጅቱ ተንብይዋል።

ከአሥር ዓመታት በላይ ወደ ድርብ አኀዝ የሚጠጋ ዕድገት ሲያሳይ የቆየው የኢትዮጵያ ምጣኔኃብት በፍጥነት እንዲያሽቆለቁል ያደረገው የተከሰተው ድርቅና የዓለምአቀፍ የሸቀጥ ገበያ ዋጋ መቀነስ እንደሆነም ጥናቱ አስረድቷል።

የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጥናት ቡድንን የመሩት ኦያ ሴላሰን በወቅቱ ምክንያቱን ሲያስረዱ “አንዱ ምክንያት ምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ብርቱ ድርቅ ተከስቶባቸዋል፤ የዝናቡ መጠን ለበርካታ ዓመታት ከተመዘገበው አማካይ በ40 ከመቶ ቀንሷል። ይሄ ሁኔታ በምጣኔኃብት ዕድገት ትንበያው ላይ ተንፀባርቋል፤ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ምጣኔኃብቶችን ጎድቷል፤ ማላዊ፣ ዚምባብዌ፣ ዛምቢያና ደቡብ አፍሪካንም ጎድቷል።" ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ድርቁ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አለመጉዳቱን መንግሥቱ አስታወቀ፤ የአይኤምኤፍ ሪፖርት ተቃራኒ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG