በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢዜማ መግለጫ እና የህወሓት ምላሽ


የኢዜማ መግለጫ እና የህወሓት ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:08 0:00

የኢዜማ መግለጫ እና የህወሓት ምላሽ

“ህወሓት ትጥቅ ባለመፍታቱ በጠብ አጫሪነቱ ቀጥሏል፤” ሲል የከሰሰው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ/ኢዜማ/ ፓርቲ፣ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላወጣው መግለጫ፣ ህሓት ምላሽ ሰጠ።

ኢዜማ፣ ባለፈው ሳምንት በራያ አላማጣ ወረዳ አካባቢ የተፈጠረውን ክሥተት በተመለከተ፣ ህወሓትን ወቅሶ ባወጣው መግለጫ፣ የፌደራሉ መንግሥት ትጥቁን በማስፈታት ሕግንና ሥርዓትን እንዲያስከብር ጠይቋል።

በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት፣ በህወሓት ጽሕፈት ቤት የፕሮፓጋንዳ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢያሱ ተስፋይ፣ ድርጅታቸው በፈረመው የፕሪቶርያው ስምምነት መሠረት በሰላማዊ መንገድ እንደሚንቀሳቀስ ገልጸዋል፡፡ በአንጻሩ ኢዜማ ክሱን ያቀረበው፣ በስምምነቱ መሠረት እየተፈጸመ ነው ያሉትን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ስለማይፈልግ ነው፤ ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕኢዜማ፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባወጣው መግለጫ፣ በራያ አላማጣ ወረዳ እና በአካባቢው የተፈጠረው የጸጥታ ችግር፣ በምርጫ ቦርድ ሕጋዊ እውቅናው የተሰረዘውና ትጥቁንም ያልፈታው ህወሓት የፈጠረው ነው፤ ሲል ከሷል፡፡

በአላማጣ እና አካባቢዋ በህወሓት ታጣቂዎች የኀይል ርምጃ እየተወሰደ እንዳለ፣ ከብዙኀን መገናኛ ባገኘው መረጃ እና በራሱ መንገድ ማጣራቱን በመግለጫው ላይ ያመለከተው ኢዜማ፣ በዚኽም የኀይል ርምጃ ብዙዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡

ፓርቲው፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚነሣባቸውን አካባቢዎች ጥያቄ፣ ህወሓት በኀይል ለመፍታት መሞከሩ የፕሪቶርያን የሰላም ስምምነት መጣሱን ያሳያል፤ ብሏል፡፡

ሌሎች ክልሎች የልዩ ኀይላቸውን አደረጃጀት ባፈረሱበት ኹኔታ፣ ህወሓት ብቻውን ታጣቂዎችን ይዞ የጠብ አጫሪነት ሥራ እየፈጸመ ይገኛል፤ ሲል የከሰሰው ኢዜማ፣ መንግሥት በፕሪቶርያው ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት መሠረት፣ ህወሓትን ትጥቅ በማስፈታት ሕግንና ሥርዓትን እንዲያስከብር በመግለጫው ጠይቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የጠየቅናቸው በህወሓት ጽሕፈት ቤት የፕሮፓጋንዳ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢያሱ ተስፋይ፣ ህወሓት በፕሪቶርያው ስምምነት መሠረት በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡በአንጻሩ፣ ኢዜማ በመግለጫው በህወሓት ላይ ያቀረበው ክስ፣ “በስምምነቱ መሠረት እየተፈጸመ ያለውን እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ከሚሠሩ አካላት አንዱ ያደርገዋል፤” ብለዋል፡፡

"በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሠረት፣ ከፌደራሉ መንግሥት ጋራ እና የአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪዎች በተገኙበት አፈጻጸሙ በየጊዜው እየተገመገመ ነው፡፡" ያሉት አቶ ኢያሱ "ከባድ እና መካከለኛ የጦር መሣሪያዎች ርክክብ ተደርጓል፡፡ ይህን እንዲያውም ህወሓት፣ በስምምነቱ ከተቀመጠው ጊዜ አስቀድሞ የፈጸመው በመኾኑ፣ ለጋራ ሰላም እንደቆመ ማሳያ ነው፡፡ የኢዜማ መግለጫ፣ ስምምነቱ ሰላማዊ መንገዱን ይዞ እንዳይቀጥል ለማደናቀፍ ከሚሠሩት መካከል ያደርገዋል" ብለዋል።

አቶ ኢያሱ ተስፋይ አያይዘውም፣ “በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሉዓላዊነታችንን ማረጋገጥና ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ማድረግ የሚሉ ጉዳዮችን አስመልክቶ በየጊዜው በህወሓት፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ በአደራዳሪዎች እና በፌደራሉ መንግሥት መግለጫዎች ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ወደ ሕገ መንግሥታዊ ግዛታችን መመለስ የሚለውን በየደረጃው ለመፍታት ኮሚቴዎች ተዋቅረዋል፡፡ በአላማጣም ይኹን በሌሎች አካባቢዎች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በስምምነቱ መሠረት የተደረጉ ናቸው፡፡ የፌደራሉ መንግሥት ሥራውን እየሠራ ነው፤ እኛም ሥራችንን እየሠራን ነን፡፡” ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት፣ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ማብራርያ የሰጡት፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕርግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባባሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፣ ኹሉም ወገኖች ካለፈው ደም አፋሳሽ ግጭት ትምህርት ወስደው የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት እንዲያከብሩ አሳስበዋል፡፡የፌደራሉ መንግሥት “አከራካሪ” እያለ የሚጠራቸው የትግራይ እና የአማራ ክልሎች አዋሳኞች የይገባኛል ጥያቄ፣ በሕግ እና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ከስምምነት መደረሱን መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG