በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮንጎ ፕሬዝደንት የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ከሀገራቸው እንዲወጣ ጠየቁ


የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቼሰኬዲ
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቼሰኬዲ

የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቼሰኬዲ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኃይል ከሀገራቸው የሚወጣበትን ሁኔታ እንዲያፋጥን መንግስታቸውን ጠይቀዋል።

ለተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት ንግግር ያደረጉት ፕሬዝደንት ቼሰኬዲ፣ ሀገራቸው ሰላም አስከባሪ ኃይሉ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ላይ መውጠት እንዲጀምር ትሻለች ብለዋል።

“በሕገ መንግስቱ በተጣለብኝ ኃላፊነት መሠረት፣ የሀገሪቱን ሉኣላዊ አንድነት እና ነጻነት እንዲሁም የሕዝቡን ደህንነት ማረጋገጥ ስላለብኝ፣ መንግስት ከተመድ ባለሥልጣናት ጋር በመነጋገር ሞኑስኮ ከኮንጎ ዲሞክርሲያዊ ሪፐብሊክ የሚወጣበትን መንገድ እንዲያፋጥን ትዕዛዝ አስተላልፊያለሁ” ብለዋል ቼሰኬዲ።

ሞኑስኮ በመባል የሚታወቀው የሰላም አስከባሪ ኃይል፣ በምሥራቅ ኮንጎ የሚታየውን ግጭት ለማርገብ፣ በ እ.አ.አ 2010 ነበር ቀደሞ ከነበረው የተመድ ልዑክ ሥራውን ተረክቦ ላለፉት 13 ዓመታት በሀገሪቱ የቆየው።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ ግን፣ ሲቪሎችን ከጥቃት አልታደገም በሚል ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል።

ባለፈው ወር በተደረገ ጸረ ተመድ ሰልፍ፣ 40 ሰዎች ሲገደሉ፣ በደርዘን የሚቆጠሩት ደግሞ ተጎድተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG