በአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ትላንት በቅድሚያ የተጫወቱት የ A ምድቦቹ አስተናጋጅ ኢኳቶሪያል ጊኒና ቡርኪና ፋሦ ያለግብ ዜሮ ለዜሮ ተለያይተዋል።
ቀጥለው የተጋጠሙት የዚሁ ምድብ ቲሞች ኮንጎ እና ጋቦን ነበሩ። በኮንጎ አንድ ለዜሮ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ዛሬ በሰባተኛው ቀን ቱኒዝያ ዛምቢያን ኡሁለት ለአንድ ቀጥታለች።
ፍልሚያው ነገና ከነገ በስቲያ ይቀጥላል። ቅዳሜ ዕለት በካሜሩንና ጊኒ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ በዋና ዳኝነት እንዲመሩ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ መመደባቸው ተገልጿል።