በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሂላሪ ክሊንተን የአዲስ አበባ ቆይታ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን በአፍሪካ ሕብረት - አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2003 ዓ.ም
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን በአፍሪካ ሕብረት - አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6/2003 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን በኢትዮጵያ ያለውን የዲሞክራሲ ሁኔታ በተመለከተ የሚደረገው ውይይት እንደሌሎቹ ዘርፎች ሁሉ በሁለቱ ሀገሮች የምክክር ማዕቀፍ ውስጥ እንዲቀጥል መግባባታቸው ተገልጧል።

በሌላ በኩል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ትናንት አዲስ አበባ ላይ በአፍሪካ ህብረት ባደረጉት ንግግር በሰሜን አፍሪካ የተቀሰቀሰው አብዮት የቀድሞዎዎቹ የአገዛዝ ሥርዓቶች ያበቃላቸው መሆኑን ያበስራሉ ብለዋል።

የአፍሪካ መሪዎች በሙሉ የሊቢያው መሪ ሞማር ጋዳፊ ሥልጣናቸውን እንዲለቁና በሀገሪቱ ዕውነተኛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ እንዲጠይቁ አበክረው ማሳሰባቸው ተዘግቧል፡፡

ዝርዝሩን መለስካቸው አምሃና እስክንድር ፍሬው ከአዲስ አበባ ካስተላለፏቸው ዘገባዎች ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG