በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጦርነት ተቃዋሚ ሰልፎች በበርሊንና በዴንቨር


ፎቶ ፋይል፦ በርሊን
ፎቶ ፋይል፦ በርሊን

በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና በህወሓት መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በአፋጣኝ እንዲቆም ግፊት እንዲደረግ የጠየቁ የትግራይ ተወላጆች ማኅበረሰቦች አባላት ጀርመን ዋና ከተማ በርሊን እና ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥም ኮሎራዶዋ ዴንቨር ከተማ ላይ ትናንት ሰልፎች አካሄደዋል።

ፍራንክፈርት የሚገኙት የትግራይ ተወላጆች ማኅበረሰቦች ጥምረት ሊቀመንበርና የሰልፉ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ግርማይ በርኸ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል በሰልፉ ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የተጓዙት የሰልፉ ተሣታፊዎች ጥያቄዎቻቸውን ለቻንስለር አንጌላ መርከል ቢሮ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ላለፉት ሃያ ስምንት ዓመታት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የዴንቨር ኮሎራዶ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሂሩት ሃጎስም ትናንት ከሺህ በላይ እንደሚሆኑ የገለጿቸው የትግራይ ተወላጆች በዴንቨር ከተማ ካፒቶል ሂል አካባቢ ሰልፍ ማድረጋቸውንና ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የአየር ድብደባውም እንዲቆም፣ የኤሌክትሪክና የስልክ አገልግሎቶች እንዲከፈቱ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። “ዋናው ጥያቄአችን ጦርነት እንደማንፈልግ እንዲታወቅልን ነው” ብለዋል።

ፌደራሉ መንግሥት “በተወሰኑ የህወሓት ባለሥልጣናት ላይ እየተካሄደ ያለ ህግን የማስከበር እንቅስቃሴ” ብሎ የሚጠራው ሲሆን የህወሓት ባለሥልጣናት ግን “በትግራይ ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው” ይላል።

ከዶ/ር ግርማይ በርኸና ከወ/ሮ ሂሩት ሃጎስ ጋር የተደረጉትን ቃለምልልሶች ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጦርነት ተቃዋሚ ሰልፎች በበርሊንና በዴንቨር
please wait

No media source currently available

0:00 0:18:20 0:00


XS
SM
MD
LG