በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከፍተኛ የዝናም እጥረት ያስከተለው ድርቅ ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ለተረጂነት የተዳረጉ አርሶ አደሮች አስታወቁ


ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመምጣቱና በአንዳንድ አካባቢወች ደግሞ ጨርሶ በመጥፋቱ ለርሃብና ለተረጂነት መዳረጋቸውን ያመለከቱት በምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች ናቸው።

በአካባቢው የሚከናወነውን የዕርዳታ ክንውን ተዘዋውሮ የተከታተለው ዘጋቢያችን እስክንድር ፍሬው፥ እነኚህ ተረጂዎች በኢትዮጵያ መንግስት ከተገለጹት 4.5 ሚሊዮን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች መካከል መሆናቸው አመልክቷል።

በሻላ ወረዳ ላይ የሚረዱት 41 ሺህ 800 እንደ ቤተሰቡ ብዛት ለአንድ ሰው 15 ኪሎ ግራም እህል እንደሚታደል፤ ይህም ሰብል እስኪደርስላቸው ለሶስት ወር የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል። በተለይም የሚያጠቡና በረሃቡ የተጎዱ እናቶች፤ በምግብ እጥረት የተጠቁ ህጻናት፤ እንዲሁም ሊወልዱ የደረሱ እናቶች አልሚ ምግብ እየታደሉ ናቸው።

XS
SM
MD
LG