በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሊቢያ የተነሱ ፍልሰተኞች ሜዲቴራኒያን ባህር ላይ ሰጥመው ሞቱ

ሊቢያን ለቀው ይጓዙ ከነበሩ ፍልስተኞች መካከል 50 የሚጠጉ ፍልሰተኞች ሜዲቴራኒያን ባህር ላይ ሰጥመው መሞታቸውን ኤስ ኦ ኤስ ሜድትሬኒያን የተባለው ነፍስ አድን ድርጅት ዛሬ ሐሙስ አስታወቀ፡፡

ባላፈው ሳምንት በሜዲቴራኒያን ባህር ላይ ከተገለበጠችው ጀልባ የተረፉት ሰዎች፣ ከሊቢያ አብረዋቸው ጉዞ ከጀመሩት 75 ሰዎች መካከል 50 የሚሆኑት የደረሱበት እንዳልታወቀ መናገራቸውን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

በባህር ላይ ቅኝት የሚያደርገው የአውሮፓ የበጎ አድራጎት ድርጅት መርከብ ትናንት ረቡዕ 25 ሰዎች የያዘችውን ትንሽ ጀልባ ተመልክቷል።

በውስጡ ከነበሩት ሰዎች መካከል ራሳቸውን የሳቱት ሁለት ሰዎች ለህክምና ወደ ጣሊያን ወታደራዊ ሆስፒታል የተላኩ ሲሆን የተቀሩት 23ቱ በከባድ ሁኔታ ላይ የሚገኙ፣ የደከሙና በጀልባዋ ላይ በነበረው ነዳጅ ፣ ቃጠሎ የደረሰባቸው እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል፡፡

የኤስ ኦ ኤስ ቃል አቀባይ ፍራንሴስኮ ክሬዞ እንደተናገሩት በህይወት የተረፉት ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ 12 የሚሆኑት ህጻናትና ሁለቱ ታዳጊ ወጣቶች ናቸው፡፡

ፍልሰተኞቹ ከሴንጋል ማሊ እና ጋምቢያ መሆናቸውም ተገልጿል። ጀልባዪቱን ተሳፍረው ከነበሩት 75 ስዎች መካከል ቢያንስ አንድ ህጻንን ጨምሮ ሴቶች ነበሩበት ተብሏል።

ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (አይ ኦ ኤም) እንደገለጸው በዚህ ዓመት እስከ መጋቢት መጀመሪያ ድረስ 227 ሰዎች አደገኛ በሆነው በማዕከላዊ ሜዲቴራኒያን ባህር ላይ ሞተዋል፡፡

ይህ በቅርቡ ሞተዋል ወይም አድራሻ ጠፍቷል የተባሉትን ሰዎች አይጨምርም። አይ ኦ ኤም እንደገለጸው በዚህ ዓመት እስከ መጋቢት 11 ድረስ 227 ሰዎች በአደገኛው መካከለኛው የሜዲቴራኒያን ባህር መስመር ላይ ሞተዋል፡፡

ካለፈው ጥር ወር መጀመሪያ ጀምሮ ተመሳሳዩን የሜዲቴራኒያን ባህር አቋርጠው ጣልያን ከገቡት 19 ሺሕ ሰዎች መካከል 279ኙ ሞተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG