በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመላ ኢትዮጵያ ስፖርት ማኅበር - /ኤሳ ዋን/ ፌስቲቫል ተጀመረ


AESA-ONE LOGO
AESA-ONE LOGO

በአሜሪካ የሚገኘው የመላ ኢትዮጵያ ስፖርት ማኅበር አምስተኛ ፌስቲቫሉን ዛሬ ጀመረ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:18 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በአሜሪካ የሚገኘው የመላ ኢትዮጵያ ስፖርት ማኅበር አምስተኛ ፌስቲቫሉን ዛሬ ጀመረ፡፡

አሌክሳንድሪያ - ቨርጂንያ ውስጥ በሚገኘው ማውንት ቬርነን ሃይ ስኩል ስታዲየም በተጀመረው በዚህ ለአንድ ሣምንት በሚዘልቀው የእግር ኳስ ግጥሚያ ላይ 18 የኢትዮጵያዊያን ቡድኖች እንደሚሣተፉ የማኅበሩ ዋና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብሥራት ገብረመስቀል ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ከአሥራ ስምንቱ ቡድኖች አሥራ ሁለቱ የአንደኛ፤ ስድስቱ የሁለተኛ ዲቪዚዮን ክለቦች መሆናቸውንም አቶ ብሥራት አመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም ሥነ-ሥርዓቱ በሚካሄድባቸው ቀናት የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ አጠቃላይ የፈተና ውጤታቸው አማካይ /ጂፒኤ/አቸው ከ3 ነጥብ ዜሮ በላይ ለሆኑ ሦስት ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው በዕጣ የአራት ሺህ ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

የኤሳ ዋን የዘንድሮ የክብር እንግዳ የፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያ የወንዶች የእግር ኳስ ክለብ የሴት አሰልጣኝ የሆነችው የድሬ ስፖርት ክለብ አሠልጣኝ መሠረት ማኒ ነች፡፡

የፊታችን ዓርብ፤ ሐምሌ 1 / 2008 ዓ.ም ፀደይ አበባ የባሕል ቡድን የሙዚቃ ዝግጅት የሚያቀርብ መሆኑንና በማግሥቱ ቅዳሜ ለዋንጫ በሚደረግ ግጥሚያ ፌስቲቫሉ እንደሚጠናቀቅ የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብሥራት ገብረመስቀል ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG