በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰላም ድርድር ሐሳቡ እና የጦርነቱ ተጎጂዎች አስተያየት


ፎቶ ፋይል፦ በጦርነቱ የተጎዳው ሀይቅ ሆስፒታል
ፎቶ ፋይል፦ በጦርነቱ የተጎዳው ሀይቅ ሆስፒታል

ወደ መቀሌ ተጉዘው የተመለሱት የዩናይትድ ስቴትስ፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኞች እና የተለያዩ ሃገሮች አምባሳደሮች ያንፀባረቁት አቋም እንዳሳዘነው የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፤

“የልዩ መልዕክተኛቹ እና የአምባሳደሮቹ ቡድን ለሠላም ውይይቱ የማያወላውል ቁርጠኝነት እንዲኖር ግፊት አላደረገም” ሲሉ ወቅሰዋል።

ይልቁን የልዑካን ቡድኑ ሌላኛውን ወገን በማባበል እና ያስቀመጣቸውን ቅድመ ሁኔታዎችም በማሟላት ተግባር ውስጥ መግባቱን በመግለጽ በሁኔታው ማዘናቸውን አስታውቀዋል።

የሠላም ውይይቱ መካሄድ ያለበትም በአፍሪካ ሕብረት መሪነት መሆን እንዳለበት ጠቅሰዋል።

መቀሌ ላይ መግለጫ የሠጡት የሕወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ተቃውሟቸው በአፍሪካ ሕብረት ላይ ሳይሆን ተቋሙ በመደባቸው ሰዎች ላይ መሆኑን አመልክተዋል።

ወደ መቀሌ ተጉዘው የተመለሱት የዩናይትድስቴትስ እና የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛች ባወጡት መግለጫ በትግራይ ክልል መብራት፣ ስልክና ባንክን የመሳሰሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች መጀመራቸው አስፈለጊ መሆኑን ገልጸዋል።

ለመሆኑ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክኒያት የተፈናቀሉ የቀጥታ ተጎጂዎች እስካሁን ባለው ሂደት ላይ ምን አስተያየት አላቸው? ትግራይ፣ አማራ እና አፋር የሚገኙ ተፈናቃዮችን ጠይቀናቸዋል።

/አስተያየታቸውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

የሰላም ድርድር ሐሳቡ እና የጦርነቱ ተጎጂዎች አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:59 0:00

XS
SM
MD
LG