በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለገዳዩ የጣፊያ ካንሰር ሕመም ዐዲስ ተስፋን የፈነጠቀ ሕክምና


 ለገዳዩ የጣፊያ ካንሰር ሕመም ዐዲስ ተስፋን የፈነጠቀ ሕክምና
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:28 0:00

የጣፊያ ካንሰር ሕመም በእጅጉ ከሚያሳስቡት የካንሰር ዓይነቶች አንዱ ነው፡፡ ሕመሙ መኖሩን ፈጥኖ ማወቅ አዳጋች በመኾኑ፣ በአመዛኙ የሚደረስበት ሥር ከሰደደ በኋላ ነው።

ለጣፊያ ካንሰር መጋለጣቸው ፈጥኖ የታወቀላቸው ሕሙማን፣ በሕክምና ጨርሶ የመፈወስ ዕድላቸው ዐሥር ከመቶ ነው፡፡ ያ ጊዜ አልፎ ዘግይቶ በሚደረስበት ወቅት ግን፣ በሕይወት ለመቆየት የሚቻልበት አማካይ ዕድሜ፣ ከሦስት እስከ ሦስት ዓመት ተኩል መኾኑን የጥናት ውጤቶች ያሳያሉ።

የምሽቱ ሐኪምዎን ይጠይቁ ትኩረት ያደረገው፣ እንዲህ ላለው ብርቱ ሕመም መፈወስ አዲስ ተስፋ በፈነጠቀ የሕክምና ዓይነት ላይ ነው።

ሞያዊ ማብራሪያውን የሚሰጡን፣ በዩናይትድ ስቴትስ የምግብ እና የመድኃኒቶች ቁጥጥር አስተዳደር የካንሰር ተመራማሪው ዶር. አሌክስ አካሉ ናቸው።

XS
SM
MD
LG