በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በወላይታ ዞን የመምህራን ደመወዝ ባለመከፈሉ ትምህርት መቋረጡ ተገለጸ


በወላይታ ዞን የመምህራን ደመወዝ ባለመከፈሉ ትምህርት መቋረጡ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:44 0:00

ላለፉት ሁለት ወራት ገደማ ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው የገለጹ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን መምህራን፣ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን አስታወቁ፡፡

ለከፋ ኢኮኖሚያዊ፣ ሥነ ልቡናዊ እና ማኅበራዊ ቀውሶች መጋለጣቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት መምህራኑ፣ አብዛኞቹም ኑሯቸውን ለመምራትና ቤተሰቦቻቸውን ለመመገብ እንደተሳናቸው አመልክተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ዐማኑኤል ጳውሎስ፣ በዞኑ ከሚገኙ ስድስት የከተማ አስተዳደሮች እና 17 ወረዳዎች ውስጥ፣ የአንድ ከተማ አስተዳደር እና የ20 ወረዳዎች መምህራን ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) ፓርቲ ደግሞ፣ ዛሬ ኀሙስ ባወጣው መግለጫ፣ ከሶዶ ከተማ አስተዳደር በስተቀር በወላይታ ዞን ሥር የሚገኙ ወረዳዎች የመንግሥት ሠራተኞች፣ ከመጋቢት እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG