በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፍልሰተኞች ላይ የደረሰ አሰቃቂ አደጋ ብሪታኒያ ያፀደቀችው የሩዋንዳ ሕግ ትኩረት እንዲስብ አድርጓል


ፍልሰተኞቹ ወደ ብሪታኒያ ጉዟቸውን ሲቀጥሉ የሚያሳይ ምስል - ሚያዚያ 23፣ 2014
ፍልሰተኞቹ ወደ ብሪታኒያ ጉዟቸውን ሲቀጥሉ የሚያሳይ ምስል - ሚያዚያ 23፣ 2014

ከፈረንሳይ የሚገቡ ጥገኝነት ፈላጊዎችን ለማስቆም የታለመውን ፍልሰተኞችን ወደሩዋንዳ የመላክ ዕቅድ የብሪታኒያ ፓርላማ ትናንት ማክሰኞ አጽድቆታል፡፡

ፓርላማው ድምጽ ከሰጠ ከጥቂት ሰዓታት በሗላ አምስት ፍልሰተኞች በጀልባ በእንግሊዝ ቻነል በኩል ለመግባት ሲሞክሩ መስጠማቸውን የፈረንሳይ ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡ ከሰጠሙት መካከል አንዷ የሰባት ዓመት ህጻን መሆኗን አመልክተዋል፡፡

ዊሜሮ ከተባለች የፈረንሳይ የባህር ዳርቻ መንደር 112 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍሮ የተነሳው የጎማ ጀልባ ጥቂት እንደተጓዘ ከተከመረ አሸዋ ጋር ተጋጭቶ በርካታ ሰዎች ወደባህሩ መውደቃቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

ጀልባዋ ላይ የቀሩ 57 የሚሆኑ ሰዎች የእርዳታ ሰራተኞች ሊያወርዱዋቸው ቢሞክሩም እምቢ ብለው በመቆየት የጀልባውን ሞተር መልሰው በማስነሳት ወደብሪታኒያ እጅግ አደገኛ የሆነውን ጉዞ ቀጥለዋል ሲሉ የፈረንሳይ ካሌ ግዛት ባለስልጣን ገልጸዋል፡፡

ፍልሰተኞች እንዲህ ባለ ከፍተኛ ቁርጠኝነት በትናንሽ ጀልባዎች በሚያደርጉት ጉዞ፣ እ አ አ በ2024 ብቻ 6 ሺህ 300 ፍልሰተኞች መግባታቸው ተገልጿል፡፡

የብሪታኒያ ፓርላማ ፍልሰተኞችን ወደሩዋንዳ ለመላክ የወጣውን ዕቅድ ትናንት ማክሰኞ ያጸደቀው ሲሆን ፍልሰተኞቹ የጥገኝነት ማማልከቻቸው ሩዋንዳ ሆነው እንደሚታይ እና የስደተኝነት ፈቃድ የሚያገኙትም ጭምር መመለስ እንደማይችሉ ተመልክቷል፡፡

የብሪታኒያ ፓርላማ ያሳለፈው ህግ ፍርድ ቤቶች ፍልሰተኞቹ ወደሩዋንዳ እንዳይላኩ ማሳገድ የሚችሉትን አሁን ስራ ላይ ያሉትን የሀገሪቱን ህግጋትም ሆነ ዓለም አቀፍ ውሎች ችላ እንዲሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG