በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሐኪሞች በእስራኤል ጥቃት ሕይወቷ ያለፈ ፍልስጤማዊ ነፍሰጡር አዋለዱ


ፍልስጤማውያን ሐኪሞች፣ በእስራኤል ጥቃት ሕይወቷ ካለፈው የ30 ሳምንት ነፍሰጡር ሴት፣ ሕፃኑን ሲያወጡ
ፍልስጤማውያን ሐኪሞች፣ በእስራኤል ጥቃት ሕይወቷ ካለፈው የ30 ሳምንት ነፍሰጡር ሴት፣ ሕፃኑን ሲያወጡ

በእስራኤል ጥቃት ሕይወቷ ካለፈ የ30 ሳምንት ነፍሰጡር ሴት፣ ሐኪሞች ሕፃኑን በቀዶ ህክምና ’ሲ ሴክሽን’ በማውጣት አዋልደዋል።

ትናንት ራፋ ላይ እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት ባልና ነፍሰጡር ሚስት እንዲሁም ሴት ልጃቸው የተገደሉ ሲሆን፣ 1.4 ኪሎግራም የሚመዝነውን ሕጻን ሐኪሞች አድነው በ’ኢንኩቤተር’ ወይም ካለ ጊዜያቸው የሚወለዱ ሕፃናት መንከባከቢያ ውስጥ አኑረዋል።

በእሁዱ የራፋ ጥቃት ሁለት መኖሪያ ቤቶች ሲመቱ፣ 19 ሰዎች መገደላቸውን፣ ከእንዚህም ውስጥ ከአንድ ቤተሰብ የሆኑ 13 ሕፃናት እንደሚገኙበት የፍልስጤማውያኑ ጤና ጥበቃ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

2.3 ሚሊዮን ከሚሆኑት የጋዛ ነዋሪ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ከጥቃቱ ለመሸሽ በራፋ ተሰባስበዋል።

እስራኤል በአሸናፊነት የምትወጣው የሐማስን ታጣቂዎች በሙሉ ስታጠፋ እንደሆነ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ተናግረዋል። በራፋ የምድር ጥቃት እንደሚያደርጉም በመዛት ላይ ናቸው።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን፣ ተጨማሪ ሲቪል ፍልስጤማውያን እንዳይጎዱ በሚል፣ እስራኤል በራፋ ላይ ጥቃት እንዳትፈጽም በማሳሳብ ላይ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG