በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በላይቤሪያ ለዕርዳታ የገባ መድሃኒት ተሰርቋል ተባለ


የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ)
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ)

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ)፤ ኤች አይ ቪ፣ ወባ እና የሳንባ በሽታዎችን ለመመርመር እና ለማከም ባለፈው ዓመት ለላይቤሪያ የለገሳቸውን 14 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ መድሃኒቶች እና ሌሎችም ቁሶች መመዝበራቸውን እና ለታሰበላቸው ዓላማ አለመዋላቸውን አስታውቋል።

የድርጅቱ የላይቤሪያ ኃላፊ የሆኑት ጂም ራይት ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ከ’ግሎባል ፈንድ’ ጋራ በመተባበር ለሃገሪቱ ባለፈው ዓመት ከተለገሰው መድሃኒት ውስጥ፣ 90 በመቶ የሚሆነው ተሰርቆ በግል ፋርማሲዎች ተሽጧል።

‘የላይቤሪያ ሕዝባዊ የጤና ተነሳሽነት’ የተሰኘውና ከዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ጋራ በመተባበር ከሚሠሩ ስድስት የሲቪል ተቋማት አንዱ ኃላፊ የሆኑት ጆይስ ኪሊክፖ ማጭበርበር መፈጸሙን አረጋግጠዋል።

የቀድሙ የሃገሪቱ የጤና ሚኒስትር በበኩላቸው፣ መድሃኒቶች ተሰርቀዋል የሚሉ ሪፖርቶች በመኖራቸው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ 90 በመቶ መድሃኒት ተሰርቋል የሚባለው ግን ከእውነታው የራቀ ነው ብለዋል። “በፋርማሲ የተገኘ መድሃኒት ሁሉ የተሰረቀ ነው ማለት አይቻልም” ሲሉም ተደምጠዋል።

የወቅቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ሉዊስ ክፖቶ ደግሞ፣ “ሁኔታዎችን እስሚረዱ ድረስ” አስተያየት እንደማይሰጡ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG