በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያና በአይ ኤም ኤፍ መካከል ልዩነቶች ቢኖሩም ድርድሩ ቀጥሏል - አይ ኤም ኤፍ


ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ)
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ)

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ለማግኘት የምትሻውን ብድር እና የኢኮኖሚ ማሻሻያን በተመለከተ ከድርጅቱ ጋራ አሁንም አንዳንድ ልዩነቶች ቢኖሩም፣ ንግግሮች ግን መቀጠላቸውን አንድ ከፍተኛ የገንዘብ ድርጅቱ ባለሥልጣን በሣምንቱ መጨረሻ አመልክተዋል።

የገንዘብ ድርጅቱን ድጋፍ ለማግኘት ኢትዮጵያ ምናልባትም የብርን የምንዛሪ ዋጋ መቀነስ እንዳለባት የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል። በአሁኑ ወቅት ብር ከዶላር ጋር በሚደረገው ምንዛሪ፣ የጥቁር ገበያው ከመንግስት ኦፊሴላዊ ምንዛሪ ዋጋ አንጻር አምሳ በመቶ በሚባል መጠን ዋጋው ቀንሶ በመመንዘር ላይ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።

የገንዘብ ድርጅቱ የብርን ዋጋ መቀነስ እንደ አንድ ቅድመ ሁኔታ እንዳስቀመጠ ባያረጋግጥም፣ በገበያ የሚወሰን እና ተለዋዋጭ የምንዛሪ ዋጋ እንዲኖር ይሻል ተብሏል።

“ድርድሮች እንደቀጠሉ ነው፣ አሁንም ልዩነቶች አሉ” ሲሉ በገንዘብ ድርጅቱ የኢትዮጵያ ኃላፊ አልቫሮ ቻቫሪ ዋሽንግተን ላይ ለሪፖርተሮች ተናግረዋል። ተስፋ እንዳለ ከጥንቃቄ ጋራ የገለጹት ኃላፊው፣ ውይይቶቹ ጊዜ ሊወስዱ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

ኃላፊው ልዩነቶቹ ምን እንደሆኑ በዝርዝር ከመግለጽ ግን ተቆጥበዋል።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትና የምንዛሪ እጥረት የገጠማት ሲሆን፣ ባለፈው ታህሳስ ደግሞ ዕዳቸውን መክፈል ካልቻሉ ሶስት የአፍሪካ ሃገራት አንዷ ሆናለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG