በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በለንደን ማራቶን ኬንያ ቀንቷታል


ኬንያዊው አሌክሳንደር ሙቲሶ ሙንያዎ የለንደኑን ማራቶን በአሸናፊነት ሲያጠናቅቅ (ፎቶ ኤፒ ሚያዚያ 21, 2024)
ኬንያዊው አሌክሳንደር ሙቲሶ ሙንያዎ የለንደኑን ማራቶን በአሸናፊነት ሲያጠናቅቅ (ፎቶ ኤፒ ሚያዚያ 21, 2024)

ኢትዮጵያዊው ቀነኒሳ በቀለ እና ኬንያዊው አሌክሳንደር ሙቲሶ ሙንያዎ ከፍተኛ ፉክክር ባደረጉበት የዛሬ ቅዳሜ የለንደን የማራቶን ውድድር፣ ኬንያዊው አትሌት ሶስት ኪሎ ሜትር ሲቀር ፍጥነቱን ጨምሮ በመገስገስ የአንደኝነቱን ድል ሲቀዳጅ፣ ቀነኒሳ በቀለ በሁለተኛነት ጨርሷል።

የሁለቱ አትሌቶች ውድድር እንደነበር በተዘገበው ማራቶን፣ ቴምስ ወንዝን በሚሻገሩበት ወቅት፣ ሙንያዎ ፈጠን በማለት የፍጻሜው ሥፍራ እስከ ሆነው በኪንግሃም ቤተመንግስት ሊመራ ችሏል። ሙንያዎ 2ሠዓት ከ4ደቂቃ ከ1ሰከንድ ሲጨርስ፣ ቀነኒሳ ከ14 ሰከንድ በኋላ የፍፃሜ መሥመሩን አቋርጧል።

የእንግሊዙ ኤሚል ኬረስ ከሶስት ደቂቃ በኋላ ገብቷል።

በመኪና አደጋ ሕይወቱ ያጣውን፣ ያለፈውን ዓመት አሸናፊ ኬንያውን ከልቪን ኪፕቱምን ለንደን በዘከረችበት በዚህ ውድድር፣ የአገሩ ልጅ ሙንያዎ፣ ድል ተቀዳጅቷል። ኪፕቱምን እያሰበ ይሮጥ እንደነበርም ሙንያዎ ተናግሯል።

የሃገሩ ልጅ ፔሬስ ጀፕችርችር በሴቶች ማራቶች አንደኛ ሆናለች። 400 ሜትር ሲቀር የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጵያዊቷን ትግስት አሰፋ ጥላ ሄዳለች፡፡ ፔሬስ ቀድማ ብትገባም፣ ያስመዘገበችው ሰዓት ግን ከትግስት አሰፋ ክብረ ወሰን 4 ደቂቃ የዘገየ ነው። ሆኖም ግን የለንደኑን ማራቶን ክብረ ወሰን ሰብራለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG