በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢራን ጥቃት ማግስት ባይደን ለእስራኤል የሚሰጡትን ድጋፍ በድጋሚ አረጋገጡ


ባይደን ቁልፍ የሀገሪቱ ተቋማት መሪዎች የሚቀመጡበት አስቸኳይ ስብሰባን ለመታደም ወደ ዋሺንግተን ቅዳሜ ጠዋት ተመልሰዋል
ባይደን ቁልፍ የሀገሪቱ ተቋማት መሪዎች የሚቀመጡበት አስቸኳይ ስብሰባን ለመታደም ወደ ዋሺንግተን ቅዳሜ ጠዋት ተመልሰዋል

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ፣ ኢራን በእስራኤል ላይ ያደረሰችውን ግዙፍ የአየር ድብደባ አውግዘው ፣ በቀጠናው የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ስምሪቶች ሁሉንም በሚባል ደረጃ በእስራኤል ላይ ተነጣጥረው የተወነጨፉ ድሮን እና ሚሳየሎችን መትቶ ለመጣል እገዛ እንዳደረጉ አስታውቀዋል ። ጥቃቱ ለስድስት ወራት የዘለቀውን እና መካከለኛው ምስራቅን ያደራሰውን ግጭት የበለጠ እንዳያስፋፋው ስጋት ፈጥሯል ።

ባይደን “አሜሪካ ለእስራኤል ደህንነት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት በድጋሚ ለማረጋገጥ” ቅዳሜ አመሻሹ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን በስልክ ማነጋገራቸውን አስታውቀዋል ።

ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዚደንት ባይደን "ለኢራን ፈር የለቀቀ ጥቃት የተባበረ ዲፕሎማሲያዊ ምላሽን ለማስተባበር" ለቡድን 7 መሪዎች የጋራ ጥሪ እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል ።

"የእኔ ቡድን በቀጠናው ከሚገኙ የእነሱ አቻ ቡድኖች ጋር ይነጋገራሉ ። ከእስራኤል መሪዎች ጋርም የቅርብ ግንኙነት ይኖረናል " ብለዋል ባይደን በመግለጫቸው ፣ " በእኛ ኃይሎችም ሆነ ተቋማት ላይ ጥቃቶችን ባንመለከተም ፣ሁሉንም ዓይነት ስጋቶችን በንቃት እንከታተላለን ። ህዝባችንን ለመከላከል ሁሉንም አይነት አስፈላጊ ርምጃዎች ለመውሰድ ወደ ኃላ አንልም " ሲሉ አክለዋል -ባይደን ።

ኢራን በእስራኤል ላይ 200 ያህል ሚሳየሎች እና ድሮኖችን ካስወነጨፈች በኃላ ባይደን ቁልፍ የሀገሪቱ ተቋማት መሪዎች የሚቀመጡበት አስቸኳይ ስብሰባን ለመታደም ወደ ዋሺንግተን ቅዳሜ ጠዋት ተመልሰዋል ።

የመጀመሪያዎች የጥቃት ምልክቶች በቀጠናው ሰማይ ላይ ከታዩ እና ከፍተኛ ድምጽ ያለው የአደጋ ጊዜ ደወል በእየሩሳሌም እና በሰሜን እስራኤል ከተሰማበት ጊዜ አንስቶ ጥቃቱ ከዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች እና ሰብዓዊ ድጋፍ ባለስልጣናት ውግዘት ተከትሎታል ።

የኢራን ባለስልጣናት በአውሮፓዊያኑ ሚያዚያ 1 እስራኤል ፣ ሶሪያ ደማሰቆ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ላይ ላደረሰቸው ጥቃት የብቀላ እርምጃ እንደሚወስዱ ቀደም ባሉት ቀናት ሲናገሩ ቆይተዋል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG