በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮረም ከተማ አስተዳደር እና የትግራይ ክልል በወታደራዊ ትንኮሳ ተካሰሱ


 የኮረም ከተማ አስተዳደር እና የትግራይ ክልል በወታደራዊ ትንኮሳ ተካሰሱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:37 0:00

ከትግራይ ክልል በኩል እየደረሰ ነው ያለው ወታደራዊ ትንኮሳ መቀጠሉን፣ የኮረም ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ ገብረ እግዚአብሔር ደረጀ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በኮረም ከተማ አከባቢዎች እና በኮረም ዙሪያ ባሉት የኦፍላ ቀበሌዎች፣ ከትግራይ ክልል በኩል የተደራጀ ወታደራዊ ኀይል ዘልቆ ገብቶ እንደነበር ጠቁመው፣ የተኩስ ልውውጦችም እንደነበሩ ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ በኮረም ከተማም ኾነ ከቀናት በፊት በአላማጣ ከተማ አስተዳደር የተሰነዘረውን ውንጀላ አይቀበሉትም። በተፃራሪው “ትንኮሳው የተፈጸመው፣ ትንኮሳው ተፈጸመብኝ ባለው አካል ነው፤” ብለዋል።

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከቤተሰብ ተለያይተው ለሁለት ዓመት ገደማ በመጠለያ ካምፕ ውስጥ መቆየታቸውን የሚናገሩ በአላማጣ ከተማ የሚኖሩ አንድ አካል ጉዳተኛ፣ ጦርነት በተለይ በአካል ጉዳተኞች፣ በሴቶች እና በሕፃናት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ተዋጊ ወገኖች ለሰላም እንዲጥሩ ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG