በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት መግለጫ በረድኤት ሠራተኞች ላይ ጫና እንደሚያሳድር ዩ.ኤስ. አይ. ዲ ገለፀ


ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች፤ እርዳታውን ከማስተባበር ይልቅ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይማተኮርን መርጠዋል ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ሰሞኑን ላሰማው ቅሬታ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩ.ኤስ. አይ. ዲ) ቃል አቀባይ ትላንት በሰጡት ምላሽ “የኢትዮጵያ መንግሥት ያሰማው ማስፈራሪያ ትግራይ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ባሉ እርዳታ አድራሽድርጅቶች ላይ ጫና ያሳድራል” ብለዋል።

ሰብዓዊ ድርጅቶች ለዕለት ደራሽ እርዳታ የሚያደርሱት በሰብዕና መርሆዎች መሰረት መሆኑን የጠቆመው የኤጀንሲው ምላሽ “እንዲህ ዓይነትመግለጫዎች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው እየሠሩ ባሉ በጎ አድራጊዎች ላይ የአደጋውን ስጋት ያባብሰዋል” ብለዋል።

መልዕክቱ እርዳታ ማድረሱን ፈታኝ እንደሚያደርገው የቃል አቀባዩ መግለጫ አመልክቷል። በጎ አድራጊዎቹ ሥራቸውን እንዳይሠሩየሚያደናቅፋቸው ማንኛውም ነገር ሕይወት የማዳኑን ሥራ ይበልጥ እንደሚያከብደውና እንዲሁም አሳሳቢ የሆነውን ሁኔያእንደሚያባብሰው አሳስቧል።

በክልሉ ውስጥ ካለው 6 ሚሊዮን ሰው 5 ሚሊዮኑ አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልገውና 900 ሺሕ የሚሆነው ሰው ለበረታ የረሃብ አደጋመጋለጡን ቃል አቀባዩ አክለው ጠቁመዋል።

ሁሉም ወገኖች የረድኤት ድርጅቶቹ መተላለፍ እንዲችሉ እንዲያደርጉ ኤጀንሲያቸው መጠየቁን እንደሚቀጥል አመላክተው፤ “እርዳታውፈጥኖ ያለማቋረጥ እና ያለመደናቀፍ መድረስ አለበት” ብለዋል።

“በተጨማሪም የነዳጅ፣ የኤሌትሪክ የቴሌኮምዩኒኬሽንስና የባንክ አገልግሎቶች ፈጥነው መመለስ ይኖርባቸዋልም” ብለዋል ቃል አቀባዩ።

በመጨረም ሁሉም ወገኖች የፀብ ሁኔታዎችን እንዲያቆሙና ተኩስ ለማቆም እንዲደራደሩ ጥሪ አሰምተዋል።

XS
SM
MD
LG