በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞት በሜዲትራንያን ባህር


ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ፍልሰተኞች ሜዲትራንያን ባህር ላይ
ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ፍልሰተኞች ሜዲትራንያን ባህር ላይ

ስደተኞችና ፍልሰተኞች በሀገሮቻቸው ከሚገጥሟቸው ግጭቶች፣ ወከባዎችና የኢኮኖሚ ችግር ሸሽተው በማዕከላዊ ሜዲትራንያን ባህር በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት የሚሞቱት ሰዎች ብዛት እየጨመረ እንደሄደ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አገልግሎቶች እየገለጹ መሆኑን ሊሳ ሽላይን ከጄኔቫ በላከችው ዘገባ ጠቁማለች።

ካለፈው ጥር ወር አንስቶ፣ አደገኛ በሆነው የማዕከላዊ ሜዲትራንያን ባህር መስመር በኩል፣ አውሮፓ ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት፣ ቢያንስ 500 የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አገልግሎቶች ጠቁሟል።

ባለፈው ዓመት በዚሁ ጊዜ ወደ አውሮፓ ለመግባት ባደረጉት ጥረት 150 ሰዎች ነበር የሞቱት።

130 የሚሆኑት ባለፈው ወር፣ በሊብያ የባህር ጠረፍ ላይ በደረሰ የመርከብ አደጋ ህይወታቸው አልፏል። ሰዎቹ ለህልፈት የተዳረጉት፣ በባህሩ የነበሩት የመድህን መርከቦች፣ አድኑን ለሚለው ጥሪያቸው፣ ምላሽ ባለመስጠታቸው ነው ሲል፣ ዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት አስገንዝቧል።

የተባበሩት መንግሥታቱ የፍልሰተኞች አገልግሎት ቃል አቀባይ ካርሎታ ሳሚ፣ ጥሩነቱ በቅርቡ በከባድ ሁኔታ ይጓዙ የነበሩ፣ 1,500 የሚሆኑ ሰዎች ያሰሙት የአድኑን ጥሪ፣ ምላሽ እንዳገኘ ተናግረዋል።

የኢጣልያ ጠረፍ ጥበቃ ክፍል፣ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ፍልሰተኞችን ከአደጋ በማትረፉ፣ ባለፈው ቅዳሜ ትራፓኒ በተባለው የሲሲሊ ወደብ፣ ለመግባት እንደቻሉ ታውቋል።

የባህር ጥበቃ የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ ባለፈው ማክሰኞ 450 ሌሎች ስደተኞችንና ፍልሰተኞችን ሲያድን በዐይናቸው ማየታቸውን፣ ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል። አብዛኖቹ ከሊብያ በደካማ ጀልባዎች የተነሱ እንደሆነና በተደጋግሚ የአድኑን ጥሪ ሲያቀርቡ እንደነበር፣ ካርሎታ ሳሚ ጠቁመዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ሞት በሜዲትራንያን ባህር
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:07 0:00


XS
SM
MD
LG