በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአረና መግለጫ እና የአማራ ክልል ምላሽ


የአረና መግለጫ እና የአማራ ክልል ምላሽ
የአረና መግለጫ እና የአማራ ክልል ምላሽ

በትግራይ ክልል በአሁኑ ሰዓት ያለውን የፀጥታ ችግር በአስቸኳይ በመቅረፍ ለሁሉም ተጎጂዎች የዕለት ደራሽምግብ እንዲያገኙ መደረግ እንዳለበት ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አሳሰበ።

በትግራይ ክልል ያለውየሰብዓዊ ቀውስ እጅግ አሳሳቢ የገለፀው ፓርቲው፤ግድያ፣ዘረፋ በሴቶች ላይ የደረሰው ወሲባዊ ጥቃት፣መፈናቀል እና ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የግዝፈታቸውን ያህል አለመነገራቸውን ገልፆ ሁኔታዎቹበአስቸኳይ እልባት ሊያገኙ ይገባል ብሏል።

በአማራ ክልል የተያዙ አካባቢዎች ሕገ መንግስቱን ተከትሎመቋጫ እስኪበጅለት ድረስ በትግራይ ክልል መስተዳደር ስር እንዲቆዩ ሲል ፓርቲው ጠይቋል።

የአማራ ክልል መንግሥት በበኩሉ፤ አማራ ክልል የያዘው ምንም ዓይነት የትግራይ ክልል እንደሌለ ገልፆ “ከዚህቀደም በሕወሓት በግዳጅ የተያዙና ነፃነታችውን የተቀሙ ነዋሪዎችን ነው ነጻ ያወጣነው” ብለዋል።

የአረና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረስላሴ እና የአማራ ክልል መንግሥት ቃል አቀባይ አቶግዛቸው ሙሉነንህ አነጋግረናል።

(ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የአረና መግለጫ እና የአማራ ክልል ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:49 0:00


XS
SM
MD
LG