በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስረኛ ፖለቲከኞችና እጩ ምዝገባ


(ፎቶ፡ አቶ ገለታው ዘለቀ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ናቸው፣የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በቴ ኡርጌሳ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እና የሕግ ባለሞያው አቶ ደበበ ኃይለገብረኤል ናቸው)
(ፎቶ፡ አቶ ገለታው ዘለቀ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ናቸው፣የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በቴ ኡርጌሳ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እና የሕግ ባለሞያው አቶ ደበበ ኃይለገብረኤል ናቸው)

በእስር ቤት የሚገኙ ፓለቲከኞች ለመጪው ምርጫ እጩ ሆነው እንዲቀርቡ እየሠራ መሆኑን ባልደራስለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አስታወቀ። አቶ ዳውድ ኢብሳ በሊቀመንበርነት የሚመሩት የኦሮሞ ነጻነትግንባር (ኦነግ) በበኩሉ አብዛኞቹ እስር ቤት የሚገኙ አባሎቹ በእጩነት እንዲመዘገቡ ጠይቋል። በዚህ ጉዳይላይ ያነጋገርናቸው የሕግ ባለሞያ ሕጉን መሰረት አድርገው ትንታኔን ሰጥተዋል።

አቶ ገለታው ዘለቀ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ናቸው። ፓርቲያቸው በአሁኑሰዓት በእስር ላይ የሚገኙ አራት አመራሮች እና አባላቱ በእጩነት ለማስመዝገብ በዝግጅት ላይ እንደሆኑገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከትላንት በስቲያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በነበረው ስብሰባ ላይ የእጩ ማስመዝገብ ሂደትን በተመለከተ ጥያቄ ተነስቶለት ነበር። ጥያቄውን ያነሱት አቶ ዳውድ ኢብሳ በሊቀመንበርነት የሚመሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በቴ ኡርጌሳ ሲሆኑ በእስር ላይ የሚገኙ አባሎቻቸውን በእጩነት ማቅረብ ስለሚችሉበት ሁኔታ ማብራሪያ ጠይቀው ነበር።

አቶ በቴ ከምርጫው ጋር በተያያይዘ ሦስት የተለያዩ ጉዳዮች እንዳነሱ ገልፀው አንደኛ የእጩዎች ጉዳይአንደኛ መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በዚሁ ስብሰባ ላይ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ በእርስ ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች ለምርጫ እጩ ሆነው መቅረብ እንደማይችሉ አስታውቀዋል።

አቶ በቴ ጥያቄዎቻቸው እስካልተመለሱ ድረስ በምርጫ የመሳተፋቸው ዕድል አነስተኛ መሆኑን በተለያየ አጋጣሚ መግለፃቸውን እና ከምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ጋር በተገናኙበት ግዜም ይህንኑ መናገራቸውንገልፀዋል።

አቶ ገለታው በበኩላቸው በሕጉ መሰረት እስረኞቹን ለምርጫ ማስመዝገብ እንደሚቀጥሉና ስለመከልከሉ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

ቦርዱ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው በእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ፣ የድጋፍ ፊርማ አሰባሰብ እና መለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 7/2013 መሰረት ሲሆን በዚህ መመሪያ፤ የእጩነት መመዘኛዎች መሰረት፤የዕጩነት ምዝገባ ጥያቄ አቀራረብ እና የምዝገባ ሥነ-ስርዓት ክፍል ላይ በሕግ ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔየመምረጥ ወይም የመመረጥ መብቱ ያልተገፈፈ ሰው እጩ ሆኖ እንደሚቀርብ ሰፍሯል።

የቦርዱ ሊቀመንበር ብርቱካን ሚዴቅሳም እንደተናገሩት እስር ቤት ቤት የሚገኝ ሰው በእጩነት ይቀርባል የሚል ሕግ የለም ነው። በፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጥያቄና የምርጫ ቦርድን አስተያየት ጠቅሰን የሕግ አስተያየት እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የሕግ ባለሞያው አቶ ደበበ ኃይለገብረኤል፤ ከምርጫ ጋር እና ተያያዥ የመምረጥ የመመረጥ መብት ጋር በተያያዘ በተለያየ ግዜ ሥልጠናዎችን በመስጠት ይታወቃሉ።

(ዘገባውን እና አቶ ደበበ የሰጡንን የሕግ ትንታኔ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

እስረኛ ፖለቲከኞችና እጩ ምዝገባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:42 0:00


XS
SM
MD
LG