በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአምነስቲ ሪፖርት በማይካድራ ጭፍጨፋ


ፎቶ ፋይል -የዳንሻ አካባቢ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ/ ሮይተርስ /ጢቅሳ ነገሪ/02/30/2013
ፎቶ ፋይል -የዳንሻ አካባቢ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ/ ሮይተርስ /ጢቅሳ ነገሪ/02/30/2013

ማይካድራ ውስጥ በመቶዎች ሲቪሎች ላይ ጭፍጨፋ ለመካሄዱ ማስረጃ እንዳለው አምነስቲ አስታወቀ።ድርጊቱ በትግራይ የፀጥታ ኃይሎች ስለመፈፀሙ መረጃዎች ያመለክታሉ ሲል ያነጋገራቸውን እማኞች ቃል ጠቅሶ በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል።የትግራይ ክልል በትግራይ ሕዝብ ላይ የተጀመረው ከባድ የዘር ማጥፋት ወረራን ለመቀጠል ሆን ተብሎ የተሰራጨ የሐሰት ዜና ነው ብሎታል። በአካባቢው የነበረ የህወሃት ልዩ ሃይልና ሚሊሻ የፈጸመው ጅምላ ጭፍጨፋ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል:

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽ ዛሬ ባወጣው አዲስሪፖርት፤ በትግራይ ክልል ደቡብ ምዕራብ ዞን በምትገኘው ማይካድራ ከተማ ውስጥበአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አስክሬኖች ማክሰኞ ዕለትመገኘታቸውን፣ ግድያውም ሕዳር ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ምሽት ላይ መፈፀሙን ማስረጃ እንዳለው አስታወቀ። በጦርነት ውስጥ ምን ተሳትፎ የሌላቸውን ሰላማዊ ዜጎችመጨፍጨፍ በጦር ወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር ነው ብሎታል።

በሌላ በኩል የማይካድራ ጭፍጨፋ የህወሃት ድርጊት ነው ያለው የአማራ ክልላዊመንግሥት በድርጊቱ የለሁበትም በሚል የሚያሰራጨውን መረጃም አጣጥሏል::

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የማይካድራ ጅምላ ግድያ በአካባቢው የነበረ የህወሃት ልዩ ሃይልናሚሊሻ የፈጸመው ጅምላ ጭፍጨፋ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል:: በአካባቢው የነበረው ብቸኛ ታጣቂ ይሄው የህወሃት ልዩ ሃይልና ሚሊሻ መሆኑን ነውየ ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታና የአስቸኳይ ጊዜ እዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃልአቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተናገሩት::

የድርጊቱ ፈፃሚ ማንነት እርቃኑን የቆመሃቅ ነው ሲሉ ነው ቃል አቀባዩ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል::

“የሚጣራ አሻሚ ጉዳይ የለም” ያሉት አምባሳደር ሬድዋን ማጣራት የሚያስፈልገውአሻሚ ጉዳይ ሲኖር ነው ብለዋል::

የአምነስቲ ሪፖርት በማይካድራ ጭፍጨፋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:48 0:00


ከዋሽንግተን፣ ከአዲስ አበባ እና ከባህርዳር የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG