በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሊባኖስ ቀውስ የውጭ ሀገር ሰራተኞችን አውላላ ሜዳ ላይ ጥሏቸዋል


የሊባኖስ ቀውስ የውጭ ሀገር ሰራተኞችን አውላላ ሜዳ ላይ ጥሏቸዋል
የሊባኖስ ቀውስ የውጭ ሀገር ሰራተኞችን አውላላ ሜዳ ላይ ጥሏቸዋል

ከቅርብ ወራት ወዲህ ሊባኖስ በተለያየ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። ህዝባዊ አመፆች፣ የኢኮኖሚ ቀውስና አሁን ደግሞ በኮሮና ምክንያት የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ አገሪቱን አስጊ ሁኔታ ውስጥ ከቷቷል። በዚህም ምክንያት ከተለያየ የዓለም ክፍል የመጡ በመቶዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ስደተኞች ችግር ላይ ወድቀዋል፣ በሊባኖስ ጎዳና ላይ የሚወድቁትም ስደተኞች ቁጥር ቀን በቀን እየጨመረ ነው። ጃኮብ ራስል ከቤሩት የላከውን ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ አጠናቅራዋለች።

በሊባኖስ፣ ከቤይሩት ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ የተጨናነቅ አውራ ጎዳና ላይ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንፅላ ፅ/ቤት ፊት ለፊት አንድ ታክሲ በጣም የተናደደችና ግራ የገባት ኢትዮጵያዊ ሴትን አወረዳት። ኢትዮጵያዊዋ ሴት በቆንፅላ ፅ/ቤቱ ዙሪያ ተጠልለው የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ተቀላቀለች።

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ፣ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ሊባኖስ ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው ከሚሰሩ 300 ሺህ ሰራተኞች መሃል ነበሩ። አሁን ግን ሊባኖስን በከፍተኛ ሁኔታ እያሽመደመዳት ባለው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ቀጣሪዎች ወጪያቸውን ለመቀነስ ሲሉ ያለምንም ማስጠንቀቂያን ዝግጅት ሰራተኞቻቸውን በማባረራቸው ሴቶቹ በየቆንስላቸው በር ላይ እንዲወድቁ ሆነዋል።

ስሟን መግለፅ የማትፈልገው ኢትዮጵያዊ፣ አሰሪዎቿ ባለፉት ሁለት ወራት የሰራችበትን ክፍያ ሳይሰጧት እንዳስወጣት ትናገራለች።

ለስደተኞቹ መብት የሚሟገት እኛ ለእኛ የተሰኘ ድርጅት ተወካይ የሆነችው መቅደስ ይልማ የሊባኖስ ቀጣሪዎች ሰራተኞቻቸውን በዚህ ሁኔታ እያስወጡ መንገድ ላይ መጣላቸው ለገንዘብ ሲባል የተደረገና ተቀባይነት የሌለው ነው ትላለች።

በሊባኖስ በፍጥነት እየተዛመተ ያለው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ቀውስ ችግሩ ገና እየተስፋፋ እንደሆነና በቅርቡ ማብቂያ እንደሌለው የሚያሳይ ነው። የፀረ-ዘረኛነት እንቅስቃሴ አቀንቃኝ የሆኑት ፋራህ ሳልካ ችግሩ በኢትዮጵያኖች ላይ በቻ ሳይሆን በሁሉም የውጪ ዜጎች ላይ የተከሰተ እንደሆነ ያስረዳሉ።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን ቤይሩት የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንፅላ ጽ/ቤት በተደጋጋሚ ብንጠይቅም መልስ አላገኘንም። ይህ ፕሮግራም እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ግን ኢትዮጵያኖቹ ሴቶች በቆንፅላው ጽ/ቤት ዙሪያ ፈሰው በማያውቁትና ችግሮች እየተባባሱ ባሉበት አገር ላይ እድላቸው ይጠብቃሉ።

የሊባኖስ ቀውስ የውጭ ሀገር ሰራተኞችን አውላላ ሜዳ ላይ ጥሏቸዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:04 0:00


XS
SM
MD
LG