ኮቪድ 19 በባህላዊ አልባሳት ሽያጭ ላይ ስለፈጠረው ጫና
የሀገር ባህል አልባሳት ተፈላጊነታቸው ከሚጨምሮባቸው ጊዜያት አንዱ የበዓላት ሰሞን ነው። በዚህ በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ የሚገኙ የባህል ልብስ መሸጫ ሱቆች ጥምቀትን የመሳሰሉ በዓዕላት ሲቃረቡ ለወትሮ በርካታ ደንበኞችን ያስተናግዱ ነበር። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተፈጠረ ወዲህ ግን የንግድ ክንውኑ ቀላል የማይባል ተግዳሮት ገጥሞታል።