ዳባት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል፤ አርባ ምንጭ ላይ ሰዎች መታሠራቸውን መኢአድ አስታውቋል፡፡ ወልድያ ላይ እሥረኞች የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡
በ2008 የበጀት ዓመት የ28 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስገባቱን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ።
ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ሁሉም የፖለቲካ ሀይሎች የሚሳተፉበት መድረክ እንዲያዘጋጁ መኢአድ ጥሪ ቀረበ።
አቶ ሆራ ፈጂሳ የተባሉ ግለስብ መገደላቸውን ባለቤታቸውም ከአራስ ልጇ ጋር በእስር ቤት እንደምትገኝ ነዋሪዎች ገለጹ።
ሰሞኑን የሥራ ማቆም አድማ ተደርጎ በነበረባቸው በጎንደርና በደብረ ማርቆስ ከተሞች ሰዉ ዛሬ፤ ረቡዕ ወደ ሥራ እየገባ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ኢትዮጵያ አስከፊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ መግባቷን በመጠቀስ ከቀውሱ ለመውጣት ኢሕአዴግ ከስልጣን ወርዶ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም የሚጠይቁ ወገኖች አሉ።
የዓለም ጤና ድርጅት ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።
ጎንደርና ደብረ ማርቆስ ውስጥ የተመታው አድማ ዛሬ፤ ማክሰኞም ቀጥሎ መዋሉን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አስታውቋል፡፡
በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶችና በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሞኑ እንቅስቃሴ ወቅት ፈጽሟል ያሏቸውን የመብት ጥሰቶች በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
በጎንደርና በደብረማርቆስ ከተሞች የሥራ ማቆም አድማ ተመትቷል፡፡
በኢትዮጵያ የተከሰተው የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታን ለመግታት መንግሥት ከዓለምአቀፍና አገር በቀል ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር እየሠራ እንደሚገኝ ታውቋል።
የመንግሥት የሀይል እርምጃ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ሀገሪቱ ወደ ከፋ ሁኔታ ልታመራ ትችላለች ሲሉ ተቃዋሚዎች አስጠንቅቀዋል።
በአማራ ክልል በደብረማርቆስ ከተማ ለተቃውሞ የወጣ ሕዝብ፣ በፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመበት መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናገሩ።
በአገሪቱ ሕልውና ላይ ያንዣበበውን ከፍተኛ አደጋ ለመከላከል ሁሉም ወገን በኃላፊነት እንዲቀሳቀስ የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)ጥሪ አቀረበ።
የኢትዮጵያ ፈዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት( መድረክ) ሰሞኑን በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ደረሰ ላለው የዜጎች እልቂት ኃላፊነቱን የሚወስደው የኢህአዲግ መንግሥት ነው አለ።
ዛሬ በሪዮ ኦሎምፒክስ የተካሄደው የሴቶች የ10ሺህ ሜትር የሩጭ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና ክብረ ወሰን በመስበር ድል ተቀናጅታለች።
በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር በመጠኑ መቀነሱን መንግሥትና አጋሮቹ አስታወቁ ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ተቃውሞ በተካሄዱባቸው አካባቢዎች ዓለምአቀፍ ገለልተኛ ታዛቢዎች እንዲገቡና እንዲመለከቱ መንግሥቱ እንዲፈቅድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጥሪ አቀረበ።
የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ አባላትና በግርግሩ ወቅት የታሠሩ ሁሉ ይፈቱ ሲል የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጥሪ አቅርቧል።
የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አራቱን ከፍተኛ የአመራር አባላት ጨምሮ ዓቃቤ ህግ በሽብር ወንጀል ክሥ የመሠረተባቸው 22 ተከሳሾች ዛሬ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
በጎንደርና በባህርዳር ከተሞች ሰላምና መረጋጋት መስፈን መጀመሩን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ። የከተሞቹ እንቅስቃሴም ወደ ቀድሞው ይዞታው እየተመለሰ እንደሆነ ገልጿል።
በአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ስናገለግል የቆየን ከ600 በላይ ሠራተኞች ከምደባ ውጭ ሆነናል ከሥራ ተባረናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ገለጹ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ቅዳሜና ዕሁድ በተካሄድ የተቃውሞ ሰልፎች የተገደለው ሰው ቁጥር ወደ መቶ እንደሚጠጋ አንዳንድ ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡
ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በኢትዮጵያ በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች በአማራና በኦሮሚያ ክልል፤ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በቀጥታ በተተኮሰ ጥይት ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን እየገለጹ ነው።
ተጨማሪ ይጫኑ