በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በየነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ የደቡብ ሱዳን መንግስትና ተቃዋሚዎቹን የማደራደር ጥረት ቀጥሏል።


please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በየነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ የደቡብ ሱዳን መንግስትና ተቃዋሚዎቹን የማደራደር ጥረት ቀጥሏል። ኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከደቡብሱዳን የሰላም ድርድር ጋር የተያያዘና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማራምደሳለኘ የተላከ ልዩ መልዕክት ለፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር አድርሰው ተመልሰዋል።
ልዩ የተባለው መልዕክት ይዘት ግን አልተብራራም። የቀሪዎቹ አራት የሱዳን መንግስት ተቃዋሚ ባለሥልጣናት ከእስር አለመፈታት ፣ ለሰላም ድርድሩ መሳካት እንቅፋት ከሆኑ ነጥቦች አንደኛው እንደሆነ ይነገራል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ ለአገር ዉስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የህዳሴ ግድብ ግንባታጋር በተያዘ የግብጽ መንግስት ላይ ሂስ ሰንዝረዋል። አቶ ዲና የግብጽባለስልጣናት የግድቡን ግንባታ ለማደናቀፍ እንደ ሩሲያ እና ታንዛኒያ ያሉ አገሮችን በመዘዋወር ለማግባባት ጥረት እያደረጉ ነዉ ሲሉ ከሰዋል።
እስክንድር ፍሬው ከአዲስ አበባ ሁለቱን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዮች አያይዞ ዘግቧል ያድምጡ።
XS
SM
MD
LG