ረቡዕ, የካቲት 10, 2016 የአካባቢው ጊዜ 09:37

  ዜና

  አና ጎመሽ - ርዕዮትና እስክንድር “የኅሊና እሥረኞች ናቸው” አሉ

  ለያዝነው የአውሮፓ 2013 ዓ.ም የአውሮፓ ፓርላማ የሳኻሮቭ ሽልማት ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሰባት ዕጩዎች ቀርበዋል፡፡

  አና ጎመሽ - የአውሮፓ ፓርላማ አባል
  አና ጎመሽ - የአውሮፓ ፓርላማ አባል  የሳኻሮቭ ሽልማት ምልክት (ሎጎ)የሳኻሮቭ ሽልማት ምልክት (ሎጎ)
  x
  የሳኻሮቭ ሽልማት ምልክት (ሎጎ)
  የሳኻሮቭ ሽልማት ምልክት (ሎጎ)

  አና ጎመሽ - ርዕዮትና እስክንድር “የኅሊና እሥረኞች ናቸው” አሉ
  አና ጎመሽ - ርዕዮትና እስክንድር “የኅሊና እሥረኞች ናቸው” አሉi
  || 0:00:00
  ...    
   
  X

  ለያዝነው የአውሮፓ 2013 ዓ.ም የአውሮፓ ፓርላማ የሳኻሮቭ ሽልማት ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሰባት ዕጩዎች ቀርበዋል፡፡

  ሽልማቱ ለሃሣብ ነፃነት ለሚታገሉና ለታገሉ የሚሰጥ የአውሮፓ ፓርላማ ዓመታዊ ክንዋኔ ነው፡፡

  ኢትዮጵያዊያኑን ዕጩዎች ርዕዮት ዓለሙንና እስክንድር ነጋን ለሽልማት ካቀረቡት አርባ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት አንዷ የፓርላማው አባል፣ እንዲሁም የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴው እና የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ አባል የሆኑት አና ጎመሽ ይገኙበታል፡፡
  ርዕዮት ዓለሙርዕዮት ዓለሙ
  x
  ርዕዮት ዓለሙ
  ርዕዮት ዓለሙ

  በአሁኑ ምርጫ ርዕዮት እና እስክንድር ቁጥራቸው ወደ 12 ከሚደርስ ከመላው ዓለም ከተጠቆሙ ሰዎች መካከል ወደ ሰባቱ አጭር ዝርዝር የገቡ መሆኑን ሚስ ጎመሽ ጠቁመው ፓርላማው የፊታችን ጥቅምት ውስጥ በሚያደርገው የተሟላ ስብሰባው ላይ አንዱ ለሽልማቱ በድምፅ እንደሚወጣ አመልክተዋል፡፡

  እስክንድርና ርዕዮት የተመረጡት ፓርላማው ባወጣው መስፈርት መሠረት የሚያደርጉት ትግል የሃገራቸው ዴሞክራሲ፣ ነፃነትና ፍትህ የለው አስተዋዖ ተመዝኖ መሆኑንም ሚስ ጎመሽ ገልፀዋል፡፡
  እስክንድር ነጋእስክንድር ነጋ
  x
  እስክንድር ነጋ
  እስክንድር ነጋ

  “እነዚህ ሰዎች እውነተኛ የሰብዓዊ መብቶች ታጋዮች ናቸው - ያሉት አና ጎመሽ ሁለቱ የኅሊና እሥረኞች ብቻ ሣይሆኑ በኢትዮጵያና በመላ አፍሪካም ለነፃነት፣ ለዴሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነት ለሚታገሉ ሁሉም ደወል ወይም መታያ ናቸው” ብለዋል፡፡

  የያዝነው የአውሮፓ ዓመት የሃሣብ ነፃነት የሳኻሮቭ ሽልማት ዕጩዎች ስሞች ለውጭ ጉዳዮች እና የልማት ኮሚቴዎቹ ጥምር ስብሰባ መቅረባቸውን የአውሮፓ ፓርላማ ያስታወቀው ከትናንት በስተያ ሰኞ ነበር፡፡

  በፓርላማው መግለጫ መሠረት ፓኪስታናዊቷ ማላላ ዩሳፍዛይ፣ አሜሪካዊው ኤድዋርድ ስኖውደን፣ ኢትዮጵያዊያኑ ርዕዮት ዓለሙ እና እስክንድር ነጋ፣ ቤላሩሲያዊያኑ አሌስ ቢያላትስኪ፣ ኤድዋርድ ላባዉ እና ማኮላ ስታትኬቪች በመላ የሃገሪቱ የፖለቲካ እሥረኞች ስም፣ ሩሲያዊው ሚኻይል ኾርዶቭስኪ፣ የቱርኩ “የቆመ ሰው” በሚል መጠሪያ የተጀመረው በቱርክ መንግሥቱ ላይ አፍጣጭ የታክሲም አደባባይ ተቃዋሚዎች ንቅናቄ የመጀመሪያው ተሰላፊ ኤርዶም ግዩንድዩዝ፣ የሲኤንኤን ቴሌቪዥን አውታር “ፍሪደም ፕሮጀክት (የነፃነት ፕሮጀክት)፡- ዘመነኛውን ባርነት ማብቃት” የሚባለው ፕሮግራም ናቸው፡፡

  ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
  ይህ ፎረም ተዘግቷል
  አስተያየቶች
       
  እዚህ ፎረም ላይ የሠፈረ አስተያየት የለም፤ የመጀመሪያው ይሁኑ