ከአምቦ እስከ መቀሌ፥}ከአዲስ አበባ እስከ ከደቡብ ህዝቦች ክልል የምርጫ ዘመቻዎች፤ ያለፈው ሳምንት መገባደጂያ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴዎች የታዩበት ነው።
የመድረኩና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አመራር አባል ዶ/ር መረራ ጉዲና ባለፈው ቅዳሜ በበርካታ ሽዎች የተቆጠሩ የአምቦና ጉደር ከተማ ነዋሪዎች የተገኙበት የምርጫ ቅስቀሳ አካሄዱ።
አረና ትግራይ በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት የጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ ተከታትለናል።
መድረክ የጠየቀው ቦታ የአዲስ አበባው መስቀል አደባባይ ስላልተፈቀደለትና
“የተጠናከረ የፖሊስ ኃይል ጥበቃ በሕዝቡ ዘንድ እንዲያጠላ አደረጓል” ባለው የፍርሃት ድባብ ሳቢያ ያቀደውን ሕዝባዊ ስብሰባ መሠረዙን መድረክ አስታወቀ።
የአሜሪካ ድምጽ በየአካባቢዎቹ ተገኝቶ ያጠናቀራቸውን ዘገባዎች ዝርዝር በተከታታይ ከዚህ ያድምጡ፤