በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫ ውጤታማ የሚሆነው አስፈፃሚዎቹ ከወገንተኝነት ሲፀዱ ነው


please wait

No media source currently available

0:00 0:11:49 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

“ምርጫ ዓለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገለጫ ነው። አንድ ሃገር ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ የሥልጣን ዝውውር ካላደረገ ዴሞክራሲያዊ ተብሎ ሊገለፅ አይችልም” ዶክተር ዓለምአንተ ገብረሥላሴ ስለ ምርጫ ምንነትና መገለጫዎቹ በሰጡትን ትንተና ነው ይህንን ያሉት።

“ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማለትም አንድ ሕዝብ በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት የሥራ ክንውኖች ጥሩውን ከመጥፎው ለይቶ የሚገመግምበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሥልጣን ይገባናል የሚሉ አዳዲስ ተወዳዳሪዎችን የፖለቲካ ፕሮግራም መርምሮ ለራሱ የሚበጀውን በማመዛዘን ውሣኔ የሚሰጥበት ሥርዓት ነው” ብለዋል ዶ/ር ዓለምአንተ።

“አንድ ምርጫ ውጤታማ የሚሆነውም የምርጫ አስፈፃሚ አካላት ከወገንተኝነት የፀዱና የዴሞክራሲያዊ ምርጫ መሥፈርቶችን ሁሉ በማሟላት ሕዝቡን ወክለው ሲሠሩና የምርጫ ውጤት ምንም ይሁን ምን ተወዳዳሪዎች የሕዝቡን ውሣኔ ሲቀበሉ ነው” ብለዋል።

ዶክተር ዓለምአንተ ገብረሥላሴ ለሃያ ዓመታት ያህል ዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂንያ ግዛት በሚገኘው ዊልያም ኤንድ ሜሪ ኮሌጅ ሕግና ሕገ መንግሥትን አስተምረዋል፡፡ አሁን ጡረታ ላይ ናቸው።

ዕሁድ፤ ግንቦት 16 ኢትዮጵያ ከምታካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ዋዜማ ትዝታ በላቸው ሰለ ነፃ ምርጫ ፋይዳና መገለጫዎቹም አነጋግራቸዋለች።

ለሙሉው ውይይት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG