በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮንሰርቲየም - ውይይት


የኢትዮጵያ ክልሎች
የኢትዮጵያ ክልሎች

ዘጠኝ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንድ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ፓርቲዎቹ ሰማያዊ ፓርቲ፣ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የከምባታ ሕዝብ ኮንግረስ፣ የመላ ኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ፓርቲ፣ የኦሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ሕብረት፣ የመላ አማራ ሕዝብ ድርጅት፣ የሶዶ ጎርደና ሕዝብ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ፣ የጌዴዖ ሕዝብ ዲሞክራቲክ ድርጅት ናቸው፡፡

አምስቱም ተቃዋሚዎች፣ ይህንኑ ስምምነት ይፋ በማድረግ ዛሬ ረቡዕ፣ በሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ፅ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በስምምነቱ መሠረትም፣ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮንሶርቲየም መመሥረቱ ታውቋል።

የኮንሶርቲየሙ አባላት በሊቀ-መንበርነት የመረጧቸው የሰማያዊ ፓርቲው ይልቃል ጌትነት እና በፀሃፊነት የተመረጡት የኦሞ ሕዝቦች ዲሞክራቲክ ሕብረቱ አቶ ግርማ በቀለ ከቪኦኤ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ቀሪዎቹ የኮንሰርቲየሙ ባለሥልጣናት ከከምባታ ሕዝብ ኮንግረስ ኤርጫፎ ኤርዴሎ ምክትል ሊቀ-መንበር፣ ከመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ካሣሁን አበባው ምክትል ዋና ፀሃፊ እና ከመላ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ኑሪ ሙደስር ዐቃቢ ነዋይ ናቸው።

የኮንሶርቲየሙ አባላት በሙሉ በመግባቢያ ሰነዱ ላይ እንደገለፁት “ካለፈው ብሔራዊ ምርጫ ጀምሮ የፖለቲካ ምኅዳሩን እያጠበበ መጥቶ እስከናካቴው በዘጋው” ባሉት ገዢ ፓርቲ ላይ ሰላማዊ ትግላቸውን በጋራ ለማጠናከር ተስማምተዋል።

መንግሥት የፖለቲካ ሰዎችን፣ የፓርቲ መሪዎችን፣ ጋዜጠኞችንና አምደኞችን ወኅኒ በማውረድ በፅኑ ላፈናቸው ለህግ የበላይነት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለሰብዓዊ መብቶች፣ ለመደራጀት፣ ሃሳብን በነፃነት ለመግለጽ መከበር እንደሚታገሉም አመልክተዋል።

የኮንሰርቲየሙን መሪዎች ከአዲሱ አበበ ያደረጉትን ውይይት የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG