በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ ወኅኒ ውስጥ አረፉ


ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ
ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ



please wait

No media source currently available

0:00 0:02:10 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የሽብር ክሥ ተመሥርቶባቸው የዕድሜ ልክ እሥራት የተፈረደባቸው ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ ለሰባት ዓመታት እሥር ላይ ከቆዩ በኋላ እዚያው ወኅኒ ውስጥ ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቪኦኤ ገለፀዋል፡፡

ፖሊስ የሰጠውን ማስረጃ አይተናል ያሉት እስከፍርዱ ድረስ ከይግባኝ በፊት ቆመውላቸው የነበሩት ጠበቃ አቶ ጥላሁን ታደሰ ኢንጂነር ተስፋሁን ያረፉት ባለፈው ዓርብ ሌሊት መሆኑን አመልክተው የፖሊሱ መረጀ እራሣቸውን ማጥፋታቸውን እንደሚጠቁም ጠቁመዋል፡፡

ኢንጂነር ተስፋሁን እራሣቸውን አጥፍተዋል የሚለውን መግለጫ ለማመን እንደሚቸገሩ የሚናገሩት አቶ ጥላሁን ታደሰ ሕክምና እንዲደረግላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ እንደነበረና የጠየቁትን አለማግኘታቸውን እንደሚያውቁ፤ ከእህታቸው ጋርም በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘው እንደነበረ ቤተሰብ እንደነገራቸው ገልፀዋል፡፡

ከወኅኒና ሌሎችም ባለሥልጣኖች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ለዛሬ ባይሳካም ሙከራችን ይቀጥላል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG