በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አራት ኢትዮጵያዊን ጋዜጠኞች የሄልማን/ሃሜት ተሸላሚ ሆኑ


Alabama, Arkanzas va Missisipida tabiiy ofat binolarni, bizneslarni yer bilan yakson qilgan.
Alabama, Arkanzas va Missisipida tabiiy ofat binolarni, bizneslarni yer bilan yakson qilgan.

አራት ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች የሚዲያ ሥራ በዓለም እጅግ አዳጋች በሆነበት ሀገራቸው ሃሣብን በነፃ የመግለፅ መብቶች እንዲከበሩ ላደረጓቸው ጥረቶች (እአአ) የ2012ን ስመ-ጥሩን የሄልማን/ሃሜትን ዓለምአቀፍ ሽልማት አግኝተዋል።




please wait

No media source currently available

0:00 0:05:38 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ድርጅት በሂዩማን ራይትስ ዋች አስተዳደር ጥላ ሥር የሚገኘው ሄልማን/ሃሜት በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የፖለቲካና ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ዒላማ ለሆኑ ደራሲዎችና ጋዜጠኞች ሽልማቱን የሚሰጠው በያመቱ ነው።
ሄልማን/ሃሜት ዓለምአቀፍ ሽልማት
ሄልማን/ሃሜት ዓለምአቀፍ ሽልማት

ስመ ጥሩ ሽልማት መጠሪያውን ያገኘው እአአ በ1950ዎቹ ፀረ-ኮሚኒስት ምርመራዎች ወቅት ወከባ ከደረሰባቸው ሁለት ጋዜጠኞች ከሊልያን ሄልማን እና ዳሸል ሃሜት ነው።

እስክንድር ነጋ

እስክንድር ነጋ ፈንታ፥ ነፃ ጋዜጠኛና ብሎገር ወይም የኢንተርኔት አምደኛ፥

ርዕዮት ዓለሙ

ርዕዮት ዓለሙ ጌቤቦ፥ በታገደው ሣምንታዊ “ፍትሕ” ጋዜጣ አምደኛ፥

ውብሸት ታየ

ውብሸት ታየ አበበ፥ የተከለከለው ሣምንታዊ “አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ፥

መስፍን ነጋሽ

የ “አዲስ ነገር Online” አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ፥ የዘንድሮውን ሽልማት ካገኙ ከ 19 ሀገሮች የተውጣጡ 41 ጋዜጠኞችና ፀሀፊዎች መካከል ናቸው።

እስክንድር፥ ርዕዮትና ውብሸት ባሁኑ ወቅ ኢትዮጵያ ውስጥ በእሥር ላይ የሚገኙ ሲሆን፥ የአዲስ ነገሩ መስፍን ነጋሽ ግን፥ እአአ በ2009 ዓ.ም ሀገሩን ጥሎ ወጥቶ በስደት ላይ ይገኛል።

ባጠቃላይ አራቱም ግን በሀገሪቱ በፀረ ሽብር ሕግ መሠረት በዚህ ዓመት ጥፋተኞች ተብለው ተፈርዶባቸዋል።

እነኚህን አራት ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ለዚህ ስመ ጥር ዓለምአቀፍ ሽልማት ያበቃቸው ምን እንደሆነ የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪቃ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል በቀለ ያስረዳሉ፡፡

እነኝህ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ባሁኑ ወቅት ለእሥርና ስደት የተዳረጉት፥ መንግሥት ሞያቸውን በነፃነት ማከናወን እንዳይችሉ ስላደረጋቸው ነው። ዛሬ ሀገሪቱ ወስጥ ባለው አፈና እራሣቸውን ተገድደው ሳንሡር ካላደረጉ፥ ቅጣት ወይም ስደት እንደሚጠብቃቸው የተደረጉትን፥ ብዙዎችን ይወክላሉ ይላል የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቱ ሂዩማን ራይትስ ዋች፡፡

እንደሌሎች በርካታ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ሁሉ፥ እስክንድር፥ ርዕዮት፥ ውብሸትና መስፍንም ብዙ መከራ ቀምሰዋል። የጋዜጠኝነት ሥራቸውን በነፃነት ለመሥራት በመሞከራቸው ብቻ በግልም በሞያቸውም ላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል ሲልም፥ ሽልማቱን የሰጣቸው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ገልጿል።

ዘገባውን ያዳምጡ
XS
SM
MD
LG