በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ያላትን የሰው-አልባ አሮፕላን ማረፊያ መዝጋቷን አስታወቀች


የአርባ ምንጭ ሰው-አልባ አሮፕላን ማረፊያ የተቋቋመው እአአ በ2011 ሲሆን፣ በሱማሌው አል-ሻባብ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ለማሰማራት እንደነበር ይታወሳል።

ዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ኢትዮጵያ አርባ-ምንጭ ውስጥ ያላትን የሰው-አልባ አሮፕላን ማረፊያ መዝጋቷን አስታወቀች።

ይህ አየር ጣቢያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በክልሉ ካላት የፀረ-ሽብርተኛነት ዘመቻ ጥረቶቿ አንዱ እንደነበር ይታወቃል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የአማሪካ ኤምበሲ ቃል-አቀባይ ካትሪን ዲዮፕ (Katherine Diop) ለአማሪካ ድምጽ አፍሪቃ ቀንድ ክፍል በላኩት ኢሜይል፥ የአርባ-ምንጩ ጣቢያ እንዲዘጋና ከእንግዲህም እንደማያስፈልግ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ኢትዮጵያ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል» ብለዋል።

የአርባ ምንጭ ሰው-አልባ አሮፕላን ማረፊያ የተቋቋመው እአአ በ2011 ሲሆን፣ በሱማሌው አል-ሻባብ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ለማሰማራት እንደነበር ይታወሳል። የዜና ዘገባ አለን ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ያላትን የሰው-አልባ አሮፕላን ማረፊያ መዝጋቷን አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:06 0:00

XS
SM
MD
LG