ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ መንግሥት እየወሰደ ያለው የኃይል እርምጃ ያሳሰባቸው መሆኑን አንድ ሌላ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባል ተናገሩ።
በምክር ቤቱ የውጭ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ አባል ሴናተር ክሪስ ኩንስ በተለይ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የኢትዮጵያ መንግሥት ይበልጥ አምባገነናዊ ወደሆነ አዝማሚያ እያመራ መሆኑን የሚጠቁም ነው፤ ሲሉም ያደረባቸውን ሥጋት ገልጠዋል።
የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተሉ መሆናቸውን የተናገሩት ሚር ኩንስ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በንግግር ነፃነት ላይ የጣላቸው ገደቦችም ሌላው አሳሳቢ ጉዳዮች ናቸው፤ ሲሉ ተችተዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡