በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመሰላ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ15 ዓመት ልጅ 11 ዓመት እስር ተፈረደበት ተባለ

ፎቶ ፋይል፡ በሂርና የነበረ ተቃውሞ
ፎቶ ፋይል፡ በሂርና የነበረ ተቃውሞ

በምዕራብ ሀረርጌ ዞን የመሰላ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኦሮሚያ ክልል ከተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በታሰሩ 13 ተከሳሾች ላይ አመፅ በማነሳሳትና ንብረት በማውደም ጥፋተኛ ናቸው ሲል የ11 ዓመት እስራት እና የገንዘብ ቅጣት ፈርዷል። ከፍርደኞቹ መካከል የ15 ዓመት ልጅና እና የስድስተኛ ክፍል ተማሪ እንደሚገኝበት ነዋሪዎቹ ይገልፃሉ።

የፍርድ ሂደቱን የተከታተሉ ቤተሰቦች ፍርደኞቹ ተማሪዎችና ገበሬዎች ሲሆኑ የታሰሩትና የተፈረደባቸውም የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በመሳተፋቸው ብቻ ነው ይላሉ ። ከፍርደኞቹ መካከል የ15 ዓመት ልጅና እና የስድስተኛ ክፍል ተማሪ እንደሚገኝበት ነዋሪዎቹ ይገልፃሉ።

የወረዳው አስተዳዳሪ ልጁም 21 ዓመቱ ነው። ፍርዱም ትክክለኛ ነው ብለዋል።

የአፋን ኦሮሞ ክፍል ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በመሰላ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ15 ዓመት ልጅ 11 ዓመት እስር ተፈረደበት ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:48 0:00

XS
SM
MD
LG